በአቅም ግንባታ ሴክተር ደጋፊ ሆነው ወደ ሙሉ ትግበራ ከተሸጋገሩ የሥራ ሂደቶች አንዱ ሥርዓተ ጾታን በልማት የማካተትና ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ የሥራ ሂደት ነው፡፡የሥራ ሂደቱ በክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ሴክተር ከተጠኑ ሁለት ዋና የስራ ሂደቶች አንዱ ሲሆን በተመረጡ የክልል ሴክተር ቢሮዎች ደጋፊ የስራ ሂደት ሆኖ ከመስከረም 2002 ዓ-ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ ተሸጋግሯል፡
በሴክተሩ በየደረጃው በሚገኝ የአመራር ቦታ፣ በሲቪል ሰርቪሱና በሌሎችም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውስጥ የሚታው የስርዓተ ጾታ ክፍተት ጠቦ ሴቶችና ወንዶች እኩል የልማት ተጠቃሚና ተሳታፊ ሆነው ማየት ነው፡፡
ሴክተሩ በሚተገብራቸው የማስፈጸም አቅም ግንባታ ፕሮግራሞችና ስትራቴጂዎች ውስጥ የሥርዓተ ጾታ ጉዳዮች በተሟላ ሁኔታ ተካቶ እንዲተገበር የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ መከታተልና መደገፍ፣
በሴክተሩ በየደረጃው በሚገኙ ዋናና ደጋፊ የስራ ሂደቶች በማናቸውም እቅዶቻቸውና የእለት ተእለት የስራ እንቅስቃሴያቸው ውስጥ የስርዓተ ጾታ ጉዳዮችን በተሟላ ሁኔታ አካተው እንዲተገብሩ ማድረግ ነው፡፡
ስልክ +25146-2-203389 /የቢሮ/ ሞባይል፣+251911760248 ፋክስ፣ +251-46-2-20-61-44 ፖስታ፣ 1157