|
|
|
Last Updated
Tuesday, February 2, 2010 3:20 PM
  |
| |
    |
| |
በልዩ ወረዳችን ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባትና ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል እየተደረጉም ይገኛል እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች የተመዘገቡ ድሎችም የህብረተሰባችንን ኑሮ ከመለወጥ አንፃር ቀላል የማይባል ለውጥ እየተዘገበ መጥቷል እነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካከል የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ አንዱ ሲሆን በየዘርፍ የተቀረፁ ፖሊሲዎች ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን በማስወገድ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ነው፡፡ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስራዎች ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታው መሣለጥ ወሳኝ በመሆናቸው በልዩ ወረዳችን ከተለያዩ መስኮች ላይ ትኩረት በማድረግ ለመንቀሳቀስ ጥረት ተደርጓል ለነዚህ ጥረቶች በርካታ ለውጦች በአፈፃፀም ረገድ የተመዘገቡ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመሠረታው የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ተጣርቶ ሙሉ ትግበራውን በጀመሩ ሴክተሮች ውስጥ የተሸለ የአገልግሎት አሰጣጥና አፈፃፀም ለውጥ እየተፈጠረ ተገልጋዩን ከሚሰጠው ግብረ መልስ መረዳት ይቻላል፡፡ አሁን እየተገበርን ያለነው የመሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ በሁለት አየር እንዲቶከርና የተፈለገውን ለውጥ እንዲያመጣ ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና ሊጫወቱ ካሥቻሉ ጉዳዮች አንዱ በየሴክተር የተመደበ የሰው ሃይል አቅም በማጎልበትና የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ማስቻል ነው፡፡ በዚህም መሠረት የልዩ ወረዳው አመራር አካላት የሲቪል ሰር ቫንት ሠራተኞቸ በተመደቡበት መደቦች የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት እንዲጨብጡ በየደረጃው የማበረታታት ስራዎችን በማከናወን የመሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ትግበራችን ተገልጋዩ የሚጠበቀውን አገልግሎት በወቅቱ በሚፈለገው መጠን በተመጣጣኝ ወጤና በተፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲያገኝ የማስቻል አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ለሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ለሚደረገው ጥረት የማስፈፀሚያ አቅም የመገንባት ስራችን ትኩረት ሠጥተን ማከናወን ይጠበቅብናል፡፡
፡ |
|
| |
| |
| |
|
  |
|
|