ሀገራችን እየተከተለች ባለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልማት ሕዝቡ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሥርዓት ለመዘርጋት ፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ በመሆኑም የልዩ ወረዳችን ሕዝብ ከሚገኝበት ኊላ ቀርነትና የድህነት ሕይወት እንዲላቀቅ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ያስመዘገባቸው የልማት ውጤቶች ዘላቂ እንዲሆኑና ቀጣይነት እንዲኖራቸው በልዩ ወረዳችን የሚታዩ የማስፈጸም አቅም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ቁልፍ የትኩረት መስክ ለይቶ ማስቀመጥ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የ5 ዓመታት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ይህንኑ ተከታትሎ የየዓመት የሴክቶሪያል ዕቅዶች ይዘጋጃሉ፡፡ ከዚህ መነሻ የአቅም ግንባታ ሴክተር የዓመት ዕቅድ ሲያዘጋጅ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመፍታት የሴክተርን ግቦች ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያልተማከለ አስተዳደርን ማጠናከር በየደረጃ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ክትትልና ግምገማ ሥርዓት በመዘርጋት የመልካም አስተዳደርን ጥያቄዎች የሚፈቱበትን ስልት ቀይሶ አጠቃላይ የሪፎርም ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ ለመተግበር ቅድሚያ ሰጥቶ የሪፎርም አስቀጣይ ተቋማትን ከመንግስት መ/ቤቶች እስከ ቀበሌ ደረጃ በራሳቸው ላይ ለውጥ ለማምጣት የማስፈጸምና የማስፈጸም አቅማቸውን መገንባት ሥራ እንዲያጎለብቱ የወረዳው አቅም ግንባታ ባለሙያዎችን በመላክ ዕገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል መንግስታዊ አገልግሎት የሚፈልገው ተገልጋይ ሕ/ሰብ በተናጥልም ሆነ በተደራጀ ሁኔታ ወደ ፈጣን ልማት እንዲገባ ማድረግ ዋነኛው የመንግስታዊ ሚና ሲሆን ይህንንም ሊያሳኩ የሚችሉ ተቋማትን የመፍጠር ሥራ የዚህ ተግባር አካል ነው፡፡ ሕ/ሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት
በጊዜና በጥራት የሚፈጸምለት ቀልጣፋና ውጤታማ ከመንግስት ተቋማት ማግኘት የዜግነት መሠረታዊ መብት በመሆኑ አገልግሎት ፈላጊው ሕ/ሰብ ከደረሰበት ማህበራዊ ጥቃትና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ብቁ ሆኖ ለመገኘት ከሚፈልገው ፍጥነትና ቅልጥፍና ጋር የሚራመድ መንግስታዊ አደረጃጀት መኖር የግድ ነው፡፡ ዘመኑ የውድድር የመሆኑን ያህል መንግስት በአገልግሎት ገበያም ውስጥ ተወዳዳሪና ተፈላጊ መሆን አለበት ፡፡ ለዚህም መሳካት አጋዥ የሆነውን ሲቨል ሰርቪስ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የድልድል ሥርዓት በመፍጠር ተገቢውን ሰው በተገቢው ቦታ በመመደብ ከየሥራ ሂደቱ የሚጠበቀውን ውጤት በማሳካት የአገልግሎት ተቀባዩን እርካታ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ነገር ግን ቀሪ ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም የለውጥ ሂደት ጋር ራስን አስማምቶና አሠራርን አጣጥሞ መሄድ አማራጭ የሌለው ይሆናል፡፡ በሌላ መልኩ ጎልቶ የሚታዩ እጥረቶችን ስለሚኖሩን ለምሳለ የበጀት ዕጥረቶች፣ የተሽከርካሪ ፣ የባለሙያ ቁጥር ማነስ፣ የኮምፒዩተር ማነስ የመሳሰሉት ፈታኝ ችግሮች ስላሉ በቀጣይ እነዚህን ቀርፈን ወደ ላቀ ደረጃ ወዳስቀመጥነው ራዕይ ግብ ለመድረስ ምቹ ሁኔታ የማስፈጸም አቅም እንደምንፈጥር ጅምር ሥራዎቻችን ምስክር በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት በጎናችን ሆነው በጋራ እንድንሠራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
|