መስከረም 20 2002ዓም>>
የዲራሼ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በአዲሱ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ መግባታቸውን ገለፀ፡፡ የልዩ ወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የለውጥ ኘርግራሞችና ኘሮጀክት ጥናት ትግበራ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አወቀ ኪታንቦ እንደገለፁት በመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመረው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ ወደሚፈለገው ግብ በአስተማማኝ አንዲደርስ ለማድረግ በየ15 ቀኑ በሴክተር/መቤቶች በመውጣት የድጋፍ ክትትል በማድረግና የክፍተት ዳሰሳ ቼክ-ሊስት በመያዝ ችግሮችን በመለየት አስፈላጊው ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ..... ተጨማሪ>>
የዲራሼ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ከ28 ቀበሌያት ለተወጣጡ ሥራ አስኪያጆችና አመራር አካላት ስልጠና መስጠቱን ገለፀ፣፡