e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Monday, December 7, 2009 11:51 PM
note

መስከረም 20 2002ዓም>>>

 new የዲራሼ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በአዲሱ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ መግባታቸውን ገለፀ፡፡

headline የዲራሼ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በአዲሱ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ መግባታቸውን ገለፀ፡፡ የልዩ ወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የለውጥ ኘርግራሞችና ኘሮጀክት ጥናት ትግበራ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አወቀ ኪታንቦ እንደገለፁት በመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመረው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ ወደሚፈለገው ግብ በአስተማማኝ አንዲደርስ ለማድረግ በየ15 ቀኑ በሴክተር/መቤቶች በመውጣት የድጋፍ ክትትል በማድረግና የክፍተት ዳሰሳ ቼክ-ሊስት በመያዝ ችግሮችን በመለየት አስፈላጊው ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ አወቀ አያይዘው በትግበራው ወቅት ችግሮች መታየታቸውን የጠቁሙ ሲሆን ለአብነትም ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት መታየት፣ አብዛኛው ሠራተኛ ስልጠና ያለመውሰድ፣ BPR በወረደው ስትሪንግ ኮሚቴ እየተመራ ያለመሆኑና ከፍተኛ የገንዘብ እጥረትና የተሽከርካሪ አለመኖር በዋናነት የሚጠቀሱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በክትትል ወቅት አበረታች ውጤቶች እየታዩ ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል አብዛኛው ጽ/ቤቱ በጥናቱ እስታንዳርድ መሠረት ሥራዎችን መጀመራቸው፣ በየስራ ሂደቱ የተዘረዘሩ ዕቅዶች መኖራቸው፣ለተገልጋዮች ግልፅ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት መጀመሩ፣ በስራው አፈፃፀም ላይ ዕለታዊ ፣ሳምንታዊ እና በየ15 ቀን የሚደረጉ ውይይቶች መጀመራቸው እና ፈጣን የቅሬታ አቤቱታ ሥነ ሥርዓት መኖሩ አበረታችና መቀጠል ያለበት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ በመጨረሻም የተጠናውን አዲሱን የስርዓት ለውጥ ሂደት በሁሉም የመንግሥት ጽ/ቤት እንደ ሥርዓት እስኪተከል ድረስ ክትትል ማድረግና ድጋፍ መስጠት የማይቋረጥና ቀጣይነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 .. . . . Next>>
Copyright © Derashe Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Derashe Special Woreda Capacity Building Website