e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Monday, December 7, 2009 11:52 PM
 
note

ነሐሴ 27 2001ዓም>>>

 new የዲራሼ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ከ28 ቀበሌያት ለተወጣጡ ሥራ አስኪያጆችና አመራር አካላት ስልጠና መስጠቱን ገለፀ

headline የልዩ ወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የሰው ሀብት ልማት አስተባባሪ አቶ ደገÕ ኪትሌ እንደገለፁት የተገልጋዮችን ፍላጐት መሠረት ያደረገ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት የተቋማትን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችል ብቃት ያለው የሰው ሀብት ለማፊራት በመልካም አስተዳደር ፖኬጅ በመሪነት ሚና ፣ የሕዝብ ግንኙነት እንፎርሜሽን ሥራ ፣ በልማት ዕቅድ ዝግጅትና በመረጃ ዙሪያ ከ22-27/12/2ዐዐ1 ዓ/ም ለ6 ቀናት ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው ከ28 ቀበሌያት የተወጣጡ 26 የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች እና 59 የቀበሌ ከፍተኛ አመራር አካላት የስልጠናው ተካፋይ ሆነዋል፡፡ አቶ ደገፋ አያይዘው ስገልፁ ከስልጠናው በኃላ ሰልጣኞች ተግባርን ከጅምሩ እስከ መጨረሻው በአነስተኛ ወጪና በተሰጠው የጊዜ ገደብ የተገልጋዩን ፍላጎት የማርካት ኃላፊነት የተጣለባቸው በመሆኑ ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎች አደራጅተው እንድጠቀሙ እንደሚያስችል እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚረዳ ሲሆን በተገኘው የደሞክራሲ ስርዓት ተጠቅሞ ልማትን እንድያፋጥኑ አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን ለየት የሚያደርገው በስልጠናው ላይ የተሳተፋ አካላቶች የሚመለከታቸውና ለአቅም መገንቢያ የሚረዳቸው በመሆኑ በፍላጐት ላይ የተመሠረተ ፣ ወቅታዊና በዕቅድ የሚመራ ቀልጣፋ ውጤታማ ወጪ ቆጣቢ በመሆኑ ለሥራቸው መሳካት ትልቅ አቅም እንደምፈጥርላቸውም ጠቁመዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 . . . . . Next>>
Copyright © Derashe Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Derashe Special Woreda Capacity Building Website