ሰኔ 30 2001ዓም>>>
በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ቀልጣፋና ደንበኞችን የሚያረካ እንደሚሆን ተገለፀ፡፡ በዲራሼ ልዩ ወረዳ ከ ሚያዚያ 1- ሰኔ 30 2001 ዓ.ም ድረስ በመሠረታዊ የኮምፒዩተር ትምህርት ሥልጠና ያገኙ 40 የመንግስት ሰራተኞች ተመረቁ፡፡ ባለፉት አመታት በመንግስት መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት ከሚሰጡ ሠራኞች መሐል የኮምፒዩተር መሠረታዊ ዕውቀት ያላቸው በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ነበሩ፡፡ ይህም በሲቪል ሰርቪስ መሥሪያ ቤቶች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ልማዳዊና በቴክኖሎጂ ያልዳበረ እንዲሆን አድርጎታል ሲሉ በዲራሼ ልዩ ወረዳ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት አቅርቦትና አገልግሎት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አሥሬ ጩፋ አስታውቀዋል፡፡ታዲያ በወረዳው የሚታየውን የመሠረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀት ችግር ለመቅረፍ ሥልጠና በመስጠት ደረጃ በደረጃ በወረዳው የሚሰጠውን የመንግስት አገልግሎት ለማሻሻል ታቅዳ_ል ሲሉ አክለዋል፡፡ ሥልጠናው አዲሱ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ሲሉ አቶ አሥሬ አስምረውበታል፡፡ በስልጠናው የተሳተፉት በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ምደባ ያገኙ ሠራተኞች የየመሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎችና የሥራ ሂደት አስተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከሠልጣኞቹ መሀል አራቱ ሴቶች ናቸው፡፡ አቶ አሥሬ አክለውም ሥልጠናው የተሰጠው ቅዳሜና እሁድ በመሆኑ በመንግስት የሥራ ሰዓት ብክነትና በአገልግሎት መዘግየት የተፈጠረ ችግር የለም ብለዋል፡፡ በዚሁ በጊዶሌ ከፍተኛ ሁለተኛና የመሰናዶ ት/ቤት የተሰጠው ሥልጠና ወደፊትም የሚቀጥል ሲሆን በያዝነው የበጀት ዓመት በሁለት ዙር 80 የመንግስት ሠራተኞች ይሰለጥናሉ፡፡ በዚሁ ፕሮግራም መሠረት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል ብለዋል አቶ አሥሬ ጩፋ፡፡ ሥልጠናውን ካገኙ ሠራኞች መሐል አቶ ጌትነት በፍቃዱ አንዱ ናቸው ፡፡ ሥልጠናውን አስመልክተው በሰጡን አስተያየት በተሠጠው ሥልጠና እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ከዚህ ቀደም ኮምፒውተር ባለበት መድረስ የማልችለው ሰውዬ አሁን በሙሉ ልብ ኮምፒዩተር ማነጋገር ችያለሁ ብለዋል ሥልጠናው በተግባር የታገዘ መሆኑ ጥሩ ክህሎት እንድናገኝ አስችላ_ል ሲሉ አቶ ጌትነት አስረድተዋል፡፡ አቶ ተገኝ ላቀውም አያይዘው በኤሌክትሪክ መቆራረጥ የተነሳ መገ_ተት ከመፈጠሩ ውጭ የሥልጠናው ሂደት በእጅጉ አስደሳች እንደነበር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኞቹ ተግባራዊ ዕውቀት እንድንገበይ ያደረጉት የነበረው ጥረት እጅግ አበረታች ነበር ብለዋል፡፡ ፕሮግራሙን ቀጣይ ለማድረግ የወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ዕቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት በያዝነው የበጀት ዓመት በ 300,000 ብር ወጪ አንድ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ይደረጋል:: ማዕከሉ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በዓመት ከ 80 በላይ የህብረተሰቡ ክፍሎች የመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉ አቶ አሥሬ ጩፋ አክለው ገልፀዋል፡፡