|
|
|
Last Updated
Sunday, February 28, 2010 7:45 PM
  |
| |
    |
| |
የኮንሶ ልዩ ወረዳ በደ/ቡ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ከሚገኙ 13 ዞኖች ፣ 8 ልዩ ወረዳዎች አንዱ ልዩ ወረዳ ነው፡፡ ልዩ ወረዳችን በስተ ደቡብ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን የደራሼ ፣ የአማሮ ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በደቡብ የኦሮሚያ ክልል/ቦረና ዞን/ ፣ በምዕራብ የደቡብ ኦሞ ዞን ፡ በምስራቅ የቡርጂ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ የልዩ ወረዳ ዋና ከተማ ካራት ሲሆን ከአዲስ አበባ 595 ኪ.ሜ እና ከክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ በ365 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ልዩ ወረዳው ለልማት አስተዳደር በሚያመች መልኩ በ48 የገጠር ቀበሌያትና በ2 የከተማ ቀበሌዎች ተዋቅሯል፡፡ በ1999 ዓ.ም በሀገር አቀፉ የህዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት የልዩ ወረዳው ህዝብ ብዛት ወንድ 116,640 ፣ ሴት 125,167 ፣ ድምር 241,802 ነው፡፡ የልዩ ወረዳችን ህብረተሰብ ከሚገኝበት ኃላቀርነትና ድህነት እንዲላቀቅ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በርካታ የልማት ውጤቶች እንደተመዘገቡ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በማህበራዊ ዘርፍ በኩል 68 የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ፡፡ 9 ታዳጊ ጤና ጣቢያና አንድ ከፍተኛ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እንዲሁም 43 ጤና ኬላዎች በጤና ዘርፍ ተሠርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በውሃ ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ በምግብ ዋስትና ዘርፍና በኢኮቴ ዘርፍ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን እነዚህን በቀጣይነት በተጀመረው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ከሚረባረቡ መንግሥታዊ ተቋማት መሀከል አንዱ የሆነው ጽ/ቤታችን ጉልህ ሚና ካለው ሴክተር አንድ ነው፡፡ ጽ/ቤታችን ካስቀመጠው ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማና እሴቶች አንፃር መልካም አስተዳደር እውን ሆነው የተጀመረው መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ለውጥ /BPR/ በሚገባ በሁሉም መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተተክሎ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ አድማስ ዳብሮና ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተጠናከረ የድጋፍ አገለግሎት ለመስጠት ከምንጊዜውም በተሻለ ደረጃ እንዲገኝ በማድረግና በዘርፉ የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት በልማት የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል በማረጋገጥ ነው፡፡
|
|
| |
| |
| |
|
  |
|
|