e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Thursday, March 4, 2010 7:52 PM
note
 

Department Headየኮንሶ ልዩ ወረዳ በደ/ቡ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ከሚገኙ 13 ዞኖች ፣ 8 ልዩ ወረዳዎች አንዱ ልዩ ወረዳ ነው፡፡ ልዩ ወረዳችን በስተ ደቡብ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን የደራሼ ፣ የአማሮ ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በደቡብ የኦሮሚያ ክልል/ቦረና ዞን/ ፣ በምዕራብ የደቡብ ኦሞ ዞን ፡ በምስራቅ የቡርጂ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ የልዩ ወረዳ ዋና ከተማ ካራት ሲሆን ከአዲስ አበባ 595 ኪ.ሜ እና ከክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ በ365 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ልዩ ወረዳው ለልማት አስተዳደር በሚያመች መልኩ በ48 የገጠር ቀበሌያትና በ2 የከተማ ቀበሌዎች ተዋቅሯል፡፡ በ1999 ዓ.ም በሀገር አቀፉ የህዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት የልዩ ወረዳው ህዝብ ብዛት ወንድ 116,640 ፣ ሴት 125,167 ፣ ድምር 241,802 ነው፡፡ የልዩ ወረዳችን ህብረተሰብ ከሚገኝበት ኃላቀርነትና ድህነት እንዲላቀቅ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በርካታ የልማት ውጤቶች እንደተመዘገቡ ይታወቃል፡፡.... ተጨማሪ>>

 
note

ጥር 29 2002ዓም>>>

 new ለሰው ሀብት መረጃና ሰታትሰቲከስ አቅርቦት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

headline በልዩ ወረዳችን በሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ ያሉ የሰው ሀብት መረጃና ሰታትሰቲከስ አቅርቦት ሰራተኞች በመሰረታዊ የሰራ ሂደት ለውጥ ና በሚሰሩዋቸው ስራዎች ላይ ሙያዊ ስልጠና ተሰጠ፡፡ አንዳንድ ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት ስልጠናው በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ላይ የነበረባቸውን የተሳሳተ አመለካከት እንደቀረፈላቸውና ለአዲሱ ስራቸውም እንደመንደርደሪያ እንደጠቀማቸው ገልፀዋል፡፡..... ተጨማሪ>>

 
ታህሳስ 18 2002ዓም>>>

new የገጠር ቀበሌ ስራ አስኪያጆች ቅጥር ለውጥ እያመጣ ነው ተባለ፡፡

headline የገጠር ቀበሌ ስራ አስኪያጆች ከዚህ በፊት በነበረው ሂደት ቋሚ ኮንትራት ሰራተኞች ስለነበርን መንግስት በፈለገው ጊዜ ሊያፈናቅለን የችላል በሚል ስራችንን በአግባቡ አናከናውንም ነበር ብለዋል፡፡አሁን ግን ቋሚ ሰራተኞች በመሆናቸው የነበረባቸው ስጋት ተወግዶ እንደማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በስራ ቀናት በስራ ቦታቸው ተገኝተው ባለጉዳዮችን ተቀብለው እንደሚያስተናግዱ ገልፀዋል፡፡..... ተጨማሪ>>
 
ህዳር 2 2002ዓም>>>
new የሲቪል ሰርቪሱ ስልጠና በጎ እምርታዎችን አያመጣ ነው ተባለ፡፡
headline የሲቪል ሰርቪሱ ስልጠና በአንዳንድ ሰራተኞች ላይ የነበረውን የአመለካከት በመቅረፍ ሠርተኛው ስራውን ከሙሉ ኃላፊነት ጋር ተቀብሎ በተጠያቂነት መንፈስ እየሰር መሆኑና ኃላፊን የመጠበቅ ሁኔታዎች መቀረፋቸውን ገልፀው ይህም ስልጠናው ያመጣው ለውጥ መሆኑን ስረድተዋል፡፡... ተጨማሪ>>
 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 . . ..... Next>>
 
የኮንሶ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት
የጽ/ቤቱ አድራሻ
ስልክ ፡- +251-46-773-0202
ፖስታ፡-
ፋክስ፡- +251-46-773-0019
ኢሜይል፡-konsocap202@yahoo.com
ካራት፣ኢትዮጵያ
 
Copyright © Konso Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Konso Special Woreda Capacity Building Website