e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Special Woreda Capacity Building Sector Offices
All Konta Woreda 44 Kebeles
Our Customers
Last Updated Tuesday, February 2, 2010 6:16 PM
 
note
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የኮንታ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት መልዕክት በአገራችን የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመዘርጋት ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ትግልና ጥረት ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም በእስካሁኑ ጥረቶች የተገኙ ድሎች በአይን የሚታዩና የምቆጠሩ ተግባሮች ናቸው ፡፡
ከእዚህም ድሎች ለአበይት ያህል በየፈርጁ የተቀረፁትን ፖሊሲ እና እስትራቴጅዎች ለማስፈፀም የሚታየውን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ የተወሰደው ርምጃዎች አንዱ ምሣሌ ሊሆን ይችላል ፡፡
የማስፈፀም አቅም ግንባታ ሥራዎች ለልማት ለዲሞክራሲና ለሠላም ጎዳናዎች ወሣኝ ሚና ሊጫወቱ ስለሚችሉ በአገራችን ብሎም በክልላችን ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ ተሰርቶበታል ፡፡ ከነዚህም አንፃር በተደረጉ ጥረቶች በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገብን ሲሆን ከነዚህም ለውጦች አንዱንና የደህነትን አረንቋ ለዘላቄታው ያቀርፋል ተብሎ የሚታመነውን የመሠረታዊ ሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ ጥናት ተጠናቆ በወረደው መሠረት በወረዳችን ከሚገኙት መ/ቤቶች በሰባቱ ሴ/መ/ቤቶች ሙሉ ትግበራውን ተከናውነው አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል ፡፡ ይህም የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ወደ መሬት ወርዶ የተፈለገውን ውጤት እንዲያስመዘግብ በየደረጃው የተመደበውን የሰው ሃይል አቅም የማጎልበትና ኃላፊነቱን ብብቃት አንዲወጣ የማስቻል ሥራ መሥራቴ ይጠበቅብናል ፡፡
በዚሁም መሠረት ይህን ተግባር ለወጡ የሚችሉ የአመራር አካላትና የሲቨል ሰርቨሲ ሠራተኞች በፖሊሲዎችና በስትራተጅዎች ላይ ግልጽነት እንዲፈጠሩ ማድረግ ወሳኝ ነው ፡፡ ይህን የሚጠቀመው አመራሩና የሲቨል ሰርቫንቱን በተመደበባቸው ቦታዎች ሥራዎችን በብቃት በመወጣት አዲሱን መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ለህብረተሰቡ የሚጠበቀውን አገልግሎት በፈለገው መጠን በተመጣጣኝ ወጪ ጥራት ያለ ሥራ እንዲሰራለት የሚያስችል አሰራር ስርዓት መዝርጋት የሚጠበቅበንን በመሆኑ ይህን ተግባር በርትተን እወጣለን ፡፡

 
 
Copyright © Konta Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Konta Special Woreda Capacity Building Website