e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Tuesday, February 2, 2010 6:09 PM
note
 
Department Head

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የኮንታ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት መልዕክት በአገራችን የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመዘርጋት ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ትግልና ጥረት ከፍተኛ ነው ፡፡ በመሆኑም በእስካሁኑ ጥረቶች የተገኙ ድሎች በአይን የሚታዩና የምቆጠሩ ተግባሮች ናቸው ፡፡ ከእዚህም ድሎች ለአበይት ያህል በየፈርጁ የተቀረፁትን ፖሊሲ እና እስትራቴጅዎች ለማስፈፀም የሚታየውን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ የተወሰደው ርምጃዎች አንዱ ምሣሌ ሊሆን ይችላል ፡፡ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ሥራዎች ለልማት ለዲሞክራሲና ለሠላም ጎዳናዎች ወሣኝ ሚና ሊጫወቱ ስለሚችሉ በአገራችን ብሎም በክልላችን ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ ተሰርቶበታል ፡፡ ከነዚህም አንፃር በተደረጉ ጥረቶች በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገብን ሲሆን ከነዚህም ለውጦች አንዱንና የደህነትን አረንቋ ለዘላቄታው ያቀርፋል ተብሎ የሚታመነውን የመሠረታዊ ሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ ጥናት ተጠናቆ በወረደው መሠረት በወረዳችን ከሚገኙት መ/ቤቶች በሰባቱ ሴ/መ/ቤቶች ሙሉ ትግበራውን ተከናውነው አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡... ተጨማሪ>>

 
note

ታህሳስ 1 2001ዓም>>

 new በኮንታ ልዩ ወረዳ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ማህበረሰቦች ለ3 ለተከታታይ ቀናትየግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጣቸው

headline ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘለቀ ዶልአሞ እንደገለጹት በከተማ ላይ ያለውን ድህነትና ስራ አጥነትን ለማስወገድ የሚቻለው የከተማ ነዋሪ በአንድነት ተደራጅቶ በመንቀሳቀስ ስለሆነ ይህ የልማታዊ መንግስት ይህንን የአደረጃጀት ስርዓት ፈጥሯል ፡፡ ከዚህም በመነሻ በጥቃቅን ና አነስተኛ እንቅስቃሴዎች ማህበር ተኪ የለሽና የመንግስት ፖሊሲና እስትራቴጂ ከግብ ለማድረስ አማራጭ የለሽ መንገድ መሆኑ ይታመናል ፡፡ ..... ተጨማሪ>>

 
ህዳር 10 2001ዓም>>>

new በኮንታ ልዩ ወረዳ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በአካባቢው በንግድ ከሚተዳደሩ ማህበረሰቦች ጋር በትናንትናው ዕለት ተወያየ፡፡

headline በውይይቱ የተነሱ የትኩረት ነጥቦች አጠቃላይ በወረዳው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችና ገቢያ ማረጋጋትን በተመለከተ ነው ፡፡ የልዩ ወረዳው ንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዶልአሞ በውይይቱ መክፈቻ እንደገለጹት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ለወረዳችን ብሎም ለሃገራችን ዕድገት የተፋጠነ ለውጥ እንድናመጣ ስለሚያስችል ሁሉም የነጋዴ ማህበረሰብ ለውይይቱ ትኩረት መስጠት አለበት ብለዋል፡፡ ..... ተጨማሪ>>
 
ህዳር 5 2001ዓም>>
new የኮንታ ልዩ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በሥራ ላይ የሚታዩ መሰረታ ችግሮችን ለማስወገድ ውጤታማ ሥራ ለመስራት መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡
headline ልማት ዲሞክራሲና አቢዮታዊ ዲሞክራሲ እንዲሁም ልማት በሲቪል ሰርቫንቱ ጥያቄ ምን ይመስላል በሚል ርዕስ የሴክተሮች ዕቅድና ፓኬጆች ላይ ለ8 ተከታታይ ቀናት አጠቃላይ ለመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከትላንት በስቲያ ተጠናቋል፡፡ በስልጠናው የተገኙት አጠቃላይ የሲቪል ሰርቫንቱ ብዛት 347 ሲሆን ወንድ 234 ሴት 113 ናቸው፡፡ የስልጠናው ተካፋይ የሆኑት አቶ አያሌው ከበደ እና ዶማንኮ ዶላንጎ ከስልጠናው ቡኃላ እንደገለጹት ለልማታችን እንቅፋት የሆነ የአፈጻጸም ችግሮች በማስወገድ ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ አለው ካሉ ቡኃላ ከስልጠናው ባገኘነው ግንዛቤ በስራችን ላይ የሚታዩ መሰረታዊ ችግሮችን አስወግደን ውጤታማ ስራ ለመስራት ተዘጋጅተናል ሲሉም ገልፀዋል ፡፡... ተጨማሪ>>
 
የኮንታ ልዩ ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት
የጽ/ቤቱ አድራሻ
ስልክ ፡-+251-47-2270022
ፖስታ፡-
ፋክስ፡- +251-47-2270349
ኢሜይል፡-
አመያ፣ኢትዮጵያ
 
Copyright © Konta Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Konta Special Woreda Capacity Building Website