በኮንታ ልዩ ወረዳ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ማህበረሰቦች ለ3 ለተከታታይ ቀናትየግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጣቸው ፡፡ ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘለቀ ዶልአሞ እንደገለጹት በከተማ ላይ ያለውን ድህነትና ስራ አጥነትን ለማስወገድ የሚቻለው የከተማ ነዋሪ በአንድነት ተደራጅቶ በመንቀሳቀስ ስለሆነ ይህ የልማታዊ መንግስት ይህንን የአደረጃጀት ስርዓት ፈጥሯል ፡፡ ከዚህም በመነሻ በጥቃቅን ና አነስተኛ እንቅስቃሴዎች ማህበር ተኪ የለሽና የመንግስት ፖሊሲና እስትራቴጂ ከግብ ለማድረስ አማራጭ የለሽ መንገድ መሆኑ ይታመናል ፡፡ በመሆኑም ይህም ውጤታማ ማድረግ የሚቻለው የከተማው ህ/ሰብ በተለይ በጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ማህበር በሰላም በልማትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች ድህነትና ስራ አጥነትን ሲሆን በተጨማሪም በአስፈፃሚ አካሎችና በአንቀሳቃሾች ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ እስከ ሂስ-ግለሂስ መድረክ በማድረግ ለቀጣይ የእርምታ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በስልጠናው ከተገኙት ውስጥ ወ/ሮ አማዝ ክንፉ አስተያየታቸውን እንደሰጡት ስልጠናው ድህነትንና ስራ አጥነትን ከከተማ ለማስወገድ መንግስት እያደረገ ያለው ጥረትና ለችግሮች መፍትሄ ለማምጣት የሚያደርገው ክትትልና ቁጥጥር በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስለተደራጀን እጅግ ያበረታታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ |