e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Tuesday, February 2, 2010 8:16 PM
 
note

ህዳር 10 2001ዓም>>>

 new በኮንታ ልዩ ወረዳ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በአካባቢው በንግድ ከሚተዳደሩ ማህበረሰቦች ጋር በትናንትናው ዕለት ተወያየ፡፡

headline በውይይቱ የተነሱ የትኩረት ነጥቦች አጠቃላይ በወረዳው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችና ገቢያ ማረጋጋትን በተመለከተ ነው ፡፡ የልዩ ወረዳው ንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዶልአሞ በውይይቱ መክፈቻ እንደገለጹት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ለወረዳችን ብሎም ለሃገራችን ዕድገት የተፋጠነ ለውጥ እንድናመጣ ስለሚያስችል ሁሉም የነጋዴ ማህበረሰብ ለውይይቱ ትኩረት መስጠት አለበት ብለዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታ የሆኑት አቶ ምንሽር ስለሺ እና አቶ መሰለ ክንፉ ከውይይቱ ቡኃላ አስተያየታቸውን እንደገለፁት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር የተወያየነው ጉዳይ በተግባር መተርጎምና የመንግስት ፖሊሲ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ለውይይቱ ከፍተኛ ግንዛቤ ያገኘንበት መድረክ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ የኮንታ ልዩ ወረዳ በትናንትናው ዕለት የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከናውኗል፡፡

በዓሉን ለማክበር ከአራት መቶ በላይ የተለያዩ የሕ/ሰብ ክፍሎች ተገኝተው በልዩ ወረዳዋ ዋና ከተማ አመያ የፀረ-ሙስናን ቀን በማስመልከት/ ሙስናን መዋጋት ከራስ ይጀምራል በሚል መርህ ቃል በፓናል ውይይት በስነ-ጹሁፍና በሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት ተከብሯል ፡፡ በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኮንታ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽብሩ እሸቱ ሙስና የአንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሃገራዊ ጉዳይ ነው ፣ ከዚያም አልፎ የመጪውን ትውልድ ዕጣ ፋንታ የሚወስን በመሆኑ የትኛውም የህ/ሰብ ክፍል መዋጋት ይጠበቅበታል ብለዋል ፡፡ በሃገራችን ሙስና አንዱ የልማት እንቅፋት በመሆኑ ጅምር ትግሎችና ስርዓቶች ቢቀመጡለትም የሚፈለገውን ያህል ለውጥ አላመጣም በመሆኑም ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ርብርብ እየተፈታተነ ይገኛል ሙስና ለሃገር ዕድገትና ልማት ለሰላምና ለመልካም አስተዳደር ትልቅ ዕንቅፋት በመሆኑ የእያንዳንዱ ዜጋ ትግል ይጠይቃል ብለዋል፡፡ በዕለቱ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት የመንግስት ሰራተኞች ፣ የከተማ ነዋሪዎች መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተው በፓናል ውይይት ላይ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ውይይት አድርገዋል ፡፡ እነዚህ የበዓሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስና ለሃገራችን እድገት ትልቅ እንቅፋት ስለሆነ ሁላችንም በጽናት በመዋጋት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 . . . Next>>
Copyright © Konta Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Konta Special Woreda Capacity Building Website