ጥቅምት 20 2001ዓም>>>
ሥልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች በመልካም አስተዳደር መርሆች፣ የፕሮጀክት ጥናት ዕቅድ ዝግጅት ትግበራ ክትትልና ግምገማ ፣ የፋይናንስ ንብረት አያያዝ ፣ዕቅድ ዝግጅት ጽንሰ ሃሳብና መረጃ አያያዝ ላይ ነው፡፡ የልዩ ወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የለውጥ ፕሮግራሞች ፕሮጀክት ጥናትና ትግበራ የሥራ ሂደት አስተባሪ አቶ ክበበው በለጠ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ስልጠናው ለችግሮች መነሻ የሆኑ መንስኤዎችን በመለየትና መፍትሄ ለመስጠት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የሥልጠናው ተካፋይ የሆኑት አቶ መኩሪያ መንገሻ እና አቶ መምህሩ መሸሻ በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው የጠራ ግንዛቤ እንዲኖረንና በቀበሌያችን ያሉትን ችግሮች ለቅመን በማውጣት የተሻለ የልማት እንቅስቃሴ እንድናደርግና ለለውጥ ለማብቃት ምንን ተከትለን መስራት እንዳለብን አቅም የሚያሳድግ ስልጠና ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡