Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Special Woreda Capacity Building Sector Offices
Our Customers
Last Updated Monday, December 14, 2009 9:56 PM
በሚቀጥለው 10 ዓመታት የልማት ኃይሎች አቅም በማጎልበት ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር፤ቀልጣፋና አገልግሎት አሠጣጥና የተፋጠነ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት በመዘርጋት ድህነት፣ኋላ ቀርነትንና ሙስና በፅናት የሚዋጋ ሕብረተሰብ በመገንባት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር ሠፍኖ ማየት፤
ተልዕኮ የአቅም ግንባታ ፖሊሲ፣ስትራቴጂና ፕሮግራሞች በመተግበር በልዩ ወረዳው የማስፈፀምና የመፈፀም ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት የዳበረ የሥራ ባሕልና ክሎት ያለው ሕብረተሰብ በመፍጠር ቀልጣፋና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ፣ ልውውጥና አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሁሉም ልማት ኃይሎች አቅም በማሳደግ የተቀናጀ ተቋማዊ አቅም እንዲፈጠር ማድረግ፡
፡
የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን የማስፈፀምና የመፈፀም ብቃት ያለው አመራር፣ሲቪል ሰርቪስ፣የሲቪክ ማህበረሰብ በመገንባት ተጠያቂነትና ኃላፊነት የሚሰማው፣ለፈጣን አገልግሎት አሠጣጥ በቁርጠኝነት የተሰለፈ፣ለዘላቂ ልማት ለመልካም አስተዳደር መስፈን አስተዋፅዖ የሚያደርግ ሕብረተሰብ እንዲፈጠር ማድረግ፡፡
የሕዝብ አገልጋይነት ስሜት መፍጠር፣
የግፀኝነትና የተጠያቂነት አሠራር መፍጠር፣
አሳታፍነት፣
ቀልጣፋና ጥራት ያለው አሠራር መፍጠር፣
ቁርጠኝነት፣
የሕግ የበላይነት ማክበር፣
አለማዳላት፣
ለመልካም አስተዳደር መስፈን የፀና እምነት መያዝ፣
ከሙስና የፀዳ አሠራር መፍጠር፣
በወረዳችን የልማትና የደሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባትና ህዝቡንም ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በተደረጉ ጥረቶችም ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በተመዘገቡት ውጤቶችም የህዝቡ ኑሮ እየተለወጠ ይገኛል፡፡ የውጤቶቹ መነሻ በአገር ደረጃ የተቀረፁና በወረዳው ውስጥ የተተገበሩት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ ነው፡፡ በስትራቴጂው የአደረጃጀት የአሠራርና የሰው ሀይል የአመለካከት የአቅም ክፍተቶች የሚሟሉበት ነው፡፡
ከላይ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሦስት የተሳሰሩ ነገሮችን ክፍተት በማሟላት ለልማትና ለደሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጎልበት የማዕዘን ድንጋይ ሆነው እንዲገኙ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በመሆኑም በአፈፃፀም ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እያስመዘገበ ነው፡፡ ዛሬ ወደሙሉ ትግበራ የተገባውም መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ እየመጣ ያለውን መሻሻል የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል በ2001 ዓ ም በተሠራው ሥራ የተሻለ አገልግሎት አሠጣጥና የአፈፃፀም ለውጥ እየተፈጠረ እንዳለ ከተገልጋዩ ከሚቀርበው አስተያየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
....
ተጨማሪ>>
Home
|
About Us
|
Departments
|
News
|
Advertisements
|
Downloads
|
Contacts
|
Photo Gallery
Copyright © Yem Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by
Webmaster
This is the Official Yem Special Woreda Capacity Building Website