e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Special Woreda Capacity Building Sector Offices
Our Customers
Last Updated Monday, December 14, 2009 10:00 PM
 
note
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በወረዳችን የልማትና የደሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባትና ህዝቡንም ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በተደረጉ ጥረቶችም ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በተመዘገቡት ውጤቶችም የህዝቡ ኑሮ እየተለወጠ ይገኛል፡፡ የውጤቶቹ መነሻ በአገር ደረጃ የተቀረፁና በወረዳው ውስጥ የተተገበሩት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ ነው፡፡ በስትራቴጂው የአደረጃጀት የአሠራርና የሰው ሀይል የአመለካከት የአቅም ክፍተቶች የሚሟሉበት ነው፡፡
ከላይ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሦስት የተሳሰሩ ነገሮችን ክፍተት በማሟላት ለልማትና ለደሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጎልበት የማዕዘን ድንጋይ ሆነው እንዲገኙ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በመሆኑም በአፈፃፀም ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እያስመዘገበ ነው፡፡ ዛሬ ወደሙሉ ትግበራ የተገባውም መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ እየመጣ ያለውን መሻሻል የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል በ2001 ዓ ም በተሠራው ሥራ የተሻለ አገልግሎት አሠጣጥና የአፈፃፀም ለውጥ እየተፈጠረ እንዳለ ከተገልጋዩ ከሚቀርበው አስተያየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጡን ተግብሮ የበቃ ለውጥ እንዲመጣ ለማድረግ ሥራውን ለመሥራት የተመደበውን የሰው ሃይል አመለካከት ለመቀየር የሚያስችል የአቅም ማጎልበት ሥራ የጎላ ድርሻ አለው፡፡ ስለዚህ በየደረጃው ያለውን ፈፃሚ በክህሎት የማብቃት ሥራ ከተሠራበት የመሠረተዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራን በተጠናው መሠረት ለተገልጋዩ አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል፡፡ ስለዚህ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥን በተሟላ እዉቀት በመምራትና በመፈፀም የህብረተሰቡን የልማትና የደሞክራሲ ሥረዓት ግንባታ ሂደት በማጎልበት በመልካም አስተዳደር መሠረታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ሁላችንም በፅናት እንሥራ፡፡

 
 
 
 
Copyright © Yem Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Yem Special Woreda Capacity Building Website