e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Monday, December 14, 2009 10:29 PM
note
 
Department Head

በወረዳችን የልማትና የደሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባትና ህዝቡንም ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በተደረጉ ጥረቶችም ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በተመዘገቡት ውጤቶችም የህዝቡ ኑሮ እየተለወጠ ይገኛል፡፡ የውጤቶቹ መነሻ በአገር ደረጃ የተቀረፁና በወረዳው ውስጥ የተተገበሩት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ ነው፡፡ በስትራቴጂው የአደረጃጀት የአሠራርና የሰው ሀይል የአመለካከት የአቅም ክፍተቶች የሚሟሉበት ነው፡፡ ከላይ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሦስት የተሳሰሩ ነገሮችን ክፍተት በማሟላት ለልማትና ለደሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጎልበት የማዕዘን ድንጋይ ሆነው እንዲገኙ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በመሆኑም በአፈፃፀም ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እያስመዘገበ ነው፡፡ ዛሬ ወደሙሉ ትግበራ የተገባውም መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ እየመጣ ያለውን መሻሻል የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል በ2001 ዓ ም በተሠራው ሥራ የተሻለ አገልግሎት አሠጣጥና የአፈፃፀም ለውጥ እየተፈጠረ እንዳለ ከተገልጋዩ ከሚቀርበው አስተያየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡.... ተጨማሪ>>

 
note

ህዳር 2 2002ዓም>>>

 new ለሁሉም የመንግስት ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ…

headline ልዩ ወረዳው ከ19 በላይ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገኙባት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ያሉ የመንግስት ሠራተኞች መደብ ያገኙም ሆነ ያላገኙ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ የልማታዊነት ጥያቄ በሲቪል ሰርቪሱ እንዴት ይመለሳል፣ ልማታዊ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሥራችን አስፈላጊነት ልማት፣ ዴሞክራሲ እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ ዙሪያ ለ442 ሲቪል ሰርቫንት ከ23/02/2002ዓ.ም ጀምሮ ለ9 ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡..... ተጨማሪ>>

 
ሚያዚያ 29 2001ዓም>>>

new ለበላይ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡

headline ለውጡን በሁለት እግር ለማስቆም የበላይ አመራሮች መለወጥ ጉልህ ሚና ስላለው የልዩ ወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በለውጥ አመራር (change management) እና በሌሎች ተዛማች ርዕሶች ላይ ሥልጠና አዘጋጅተው ለ30 የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ም/ኃላፊዎች፣ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎች ከሚያዝያ 29/2001 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ተሰጠ፡፡..... ተጨማሪ>>
 
ሚያዚያ 15 2001ዓም>>>
new ለቀበሌ ሥራ አስኪያጆቸና አፈ-ጉባኤዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
headline በልዩ ወረዳው 32 የገጠር ቀበሌዎችና 2 የከተማ ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በ32ቱ ቀበሌዎች ላይ ተቀጥረው እያገለገሉ ላሉ ሥራ አስኪያጆችና አፈ-ጉባኤዎች ም/አፈ-ጉባኤዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነ ከሚያዝያ 15/2001 ዓ.ም ጀምሮ ለገጠር ቀበሌ ሥራ አስኪያጆች አፈ-ጉባኤዎች ም/አፈ-ጉባኤዎች በመሪነት፣ በገንዘብና ንብረት አያያዝ፣ በሪፖርት ዝግጅትና ግብረ-መልስ ዙሪያ ለ3 ተከታታይ ቀ ናት ሥልጠና ተሰጠ፡፡... ተጨማሪ>>
 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 . . ..... Next>>
 
 
 
Copyright © Yem Special Woreda CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Yem Special Woreda Capacity Building Website