Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Dawero Zone Capacity Building Sector Departments
All Dawero Zone Woreda Capacity Building Offices
Dawero Development Associations
Our Customers
Last Updated Thursday, November 26, 2009 3:51 PM
በዞኑ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ድህነትንና ኋላቀርነትን በመዋጋት ፣በመልካም አሰተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ሥነ ምግባር የታነፀ ብቃት ያለው ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ተገንብቶ ማየት፡
የአቅም ግንባታ ፖሊሲን ስትራቴጂና ፕሮግራሞችን በመተግበር ዘላቂ ልማት በማምጣት የድህነት ቅነሳ ግብን ማሳካት የሚችል ህብረተሰብ እንዲፈጠር ማድረግ
በዞኑ መልካም እስተዳደርን ለማስፈን ፣ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት እንዲሁም
ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትንና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት
ሲቪል ሰርቪሱ ቁልፍ ሚና በመጫወት የተገልጋይን ማህበረሰብ ፍላጎት እንዲያረካ ማስቻል፣
የዞናችን መንግስት የልማት ቁልፍ መሣሪያ የሆነውን የማስፈጸም አቅም በመገንባት መልካም አስተዳደርን በሁሉም ደረጃ ለማረጋገጥ የሚችል የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ፤በአሠራር ፣በአደረጃጀትና በሠለጠነ የሠው ኃይል አካባቢ የሚታየውን ቁልፍ ችግር ሲቀርፍ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካትና የሚጠበቅበውን ውጤት ማስመዝገብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በየጊዜው የተገልጋዩን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የአሠራር ፣የአደረጃጀትና በአመለካከት የተለወጠ የሠው ኃይል እንዲኖር የማሻሻል ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም ከጊዜ ፣ከወጪ፣ ከጥራትና ከተገልጋይ እርካታ አንጻር በቂ ውጤት አልተገኘም፡፡ ስለሆነም ይህን ችግር ለመቅረፍ በሚያሥችል መልኩ በተመረጡ ሰባት ሴክተር መ/ቤቶች መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት የሙከራ ትግበራ ውጤታማነቱ ተረጋግጦ ወደሙሉ ትግበራ መግባት የሚያስችል የሠራተኞች ድልድል ደንብ ቁጥር 72/2001 እና የትግበራ ስትራቴጂ ፀድቆ የሠራተኞች ድልድል ከተካሄደ በኋላ ሥልጠና ተሰጥቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ መምሪያችንም ይህን ትግበራ በቀዳሚነት ከጀመሩት ሰባት ሴክተሮች አንዱ ሲሆን አራት ዋና የሥራ ሂደቶች ተለይተው የግብ ስኬት ላይ ያተኮረ የአሠራር ሥርዓት የተቀረጸላቸው ሲሆን በፋ/ኢ/ልማት የተጠኑ ሁለት ደጋፊ የሥራ ሂደቶችን አካትቶ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠቱም በላይ ሌሎችን ሴክተሮች የማስተባባርና የመደገፍ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
....
ተጨማሪ>>
Home
|
About Us
|
Departments
|
News
|
Advertisements
|
Downloads
|
Contacts
|
Photo Gallery
Copyright © Dawero Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by
Webmaster
This is the Official Dawero Zone Capacity Building Website