e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Dawero Zone Capacity Building Sector Departments
All Dawero Zone Woreda Capacity Building Offices
Dawero Development Associations
Our Customers
Last Updated Thursday, November 26, 2009 3:56 PM

የማስፈጸም አቅም የልማት ዋነኛ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የልማት ዋነኛ ውጤትም ጭምር ነው!!!

 
note
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የዞናችን መንግስት የልማት ቁልፍ መሣሪያ የሆነውን የማስፈጸም አቅም በመገንባት መልካም አስተዳደርን በሁሉም ደረጃ ለማረጋገጥ የሚችል የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ፤በአሠራር ፣በአደረጃጀትና በሠለጠነ የሠው ኃይል አካባቢ የሚታየውን ቁልፍ ችግር ሲቀርፍ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካትና የሚጠበቅበውን ውጤት ማስመዝገብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በየጊዜው የተገልጋዩን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የአሠራር ፣የአደረጃጀትና በአመለካከት የተለወጠ የሠው ኃይል እንዲኖር የማሻሻል ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም ከጊዜ ፣ከወጪ፣ ከጥራትና ከተገልጋይ እርካታ አንጻር በቂ ውጤት አልተገኘም፡፡ ስለሆነም ይህን ችግር ለመቅረፍ በሚያሥችል መልኩ በተመረጡ ሰባት ሴክተር መ/ቤቶች መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት የሙከራ ትግበራ ውጤታማነቱ ተረጋግጦ ወደሙሉ ትግበራ መግባት የሚያስችል የሠራተኞች ድልድል ደንብ ቁጥር 72/2001 እና የትግበራ ስትራቴጂ ፀድቆ የሠራተኞች ድልድል ከተካሄደ በኋላ ሥልጠና ተሰጥቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ መምሪያችንም ይህን ትግበራ በቀዳሚነት ከጀመሩት ሰባት ሴክተሮች አንዱ ሲሆን አራት ዋና የሥራ ሂደቶች ተለይተው የግብ ስኬት ላይ ያተኮረ የአሠራር ሥርዓት የተቀረጸላቸው ሲሆን በፋ/ኢ/ልማት የተጠኑ ሁለት ደጋፊ የሥራ ሂደቶችን አካትቶ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠቱም በላይ ሌሎችን ሴክተሮች የማስተባባርና የመደገፍ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡

በዞኑ በተመረጡ ሰባት ሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ ሰላሳ አራት የሥራ ሂደቶች ሥር ነቀል ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ከጥር ወር 2001 ጀምሮ ሙሉ ትግበራ የተገባ ሲሆን በዚህ ረገድ የሥራ ሂደቶች ተደራሽ ግቦችን /stretch objectives/ ማሳካታቸውን፣አሮጌ አሰራሮችና አስተሳሰቦች በአዲስ መተካታቸውን፣ የሥራ ሂደቱ በተጠናው መሠረት መተግበሩን፣ለተገልጋይ እርካታ እያስገኘ መሆኑን፣በትግበራው ወቅት ላጋጠሙ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ መሠጠቱንና በየደረጃው ባሉት አካላት የክትትልና ግምገማ ተግባራት መከናወናቸውና ግብረ-መልስ በተገቢው ሁኔታ መሰጠቱ የመምሪያችን ተልዕኮ ሲሆን በየጊዜውም ለየሴክሮቹ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በ2ኛው ዙር ወደሙሉ ትግበራ የሚገቡ ሴክተሮች ለትግበራው ቅድመ-ዝግጅት እንዲያደርጉ የጋራ ውይይት በማድረግ የቢሮና መስሪያ አካባቢ ዝግጅት፣ቁሳቁስና ከቀደሙት የተሞክሮ ልውውጥ የሚካሄድበት ሁኔታ በኮሚቴ ተጠንቶ ለአስ/ር ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ከሁሉም በላይ በጥናቱ መሠረት ሲቪል ሰርቪሱ ቀልጣፋ፣ውጤታማ፣ቀጣይነትና የአሰራር ግልጽነት ያለውና የልማት አጋዥ እንዲሆንና ሥራው ለውጥን ውድድርን ደንበኛን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ጠቀሜታውን ህዝቡ እንዲያውቀው ማስረዳት ይገባል፡፡ይህም በህዝቡ ድጋፍና ባለቤትነት ፈጣን ፣ወጪ ቆጣቢ ልማትን ሊያሣልጥለት የሚችል አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርገዋልና፡፡

ስለሆነም በየደረጃው ያለው አመራር ለትግበራው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣በበቂ ዕውቀት መምራት የሥራ ሂደት አስ/ሪዎች/ባለቤት ማብቃትና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት ፣ተከታታይ ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣ቀልጣፋ የግንኙነት ሥርዓት ዘርግቶ ሠራተኞች ለውጡን እንዲቀበሉና እንዲደግፉ ጠንካራ የለውጥ አመራር ሥራዎችን መስራትና ለትግበራው የተሰጠ አርዓያነትና ቁርጠኝነት ማሳየት ይጠበቃል፡፡ሠራተኛውም ለውጡን ከማሳካት አንጻር ንቁና ተግባራዊ ተሳትፎ ማድረግ፣ገንቢ ግብዓቶችን መስጠት ለውጡን ከልብ ደግፎ መሥራትና አዲሱ የሥራ ሂደት በተቀረፀውና በተደራጀው ሁኔታ መተግበር ግድ ይላል፡፡

በአጠቃላይ በለውጡ ሂደት ሚና ያላቸው አካላት በሙሉ ትግበራ ወቅት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑና የለውጡን ሂደት አደናቃፊ የሆኑ ጉደዮችን ለይቶ ችግሩን በመፍታት ለውጡን እውን ማድረግና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል እላለሁ፡፡

ለልማታችን ግብ ስኬት
መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ
ወሳኝ ሚና አለው፡

 
 
Copyright © Dawero Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Dawero Zone Capacity Building Website