e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Dawero Zone Capacity Building Sector Departments
All Dawero Zone Woreda Capacity Building Offices
Dawero Development Associations
Our Customers
Last Updated Friday, December 4, 2009 8:34 PM

የማስፈጸም አቅም የልማት ዋነኛ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የልማት ዋነኛ ውጤትም ጭምር ነው!!!

note

የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የአፈጻጸም ከፍተትን መለየት፤
  • ጥናት እንዲካሄድና የማስፈጸም ሰነድ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
  • በፓይለት የተፈተሸ የማስፈጸሚያ ሰነድ መረከብ፤
  • የትግበራ ዕቅድ ማዘጋጀትና ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤
  • የትግበራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
  • የፋይዳ ግምገማ ማድረግ፤
  • የጥናት ሥራውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
  • የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራሞችንና የሪፎርም ተግባራትን ይመራል፤ይደግፋል፤ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤

በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት

  1. የሥራ ሂደቱ አስተባባሪና የፕሮጄክት ዕቅድ ክትትል ግምገማ ባለሙያ(2)
 
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-
  • ተጠንተው የተወሰኑ የሥራ ደረጃና ጥቅማ ጥቅሞችን በመስፈርቱ መሰረት ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ
  • የሠው ሃብት ፍላጎትና ዕቅድ ማዘጋጀት
  • በቅጥር ፤በዝውውር እና በደረጃ እድገት የሰው ሃብት ማሟላት፤መመዝገብ
  • ፈቃድ በፕሮግራሙ መሰረት መፈጸሙን ማረጋገጥ
  • የሥራ ሂደቶችን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ውጤቶችን ማሰባሰብ፤ማደራጀትና ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ
  • የዲስፕሊን ርምጃ መውሰድ
  • የድጋፍ ፤የክትትልና ምክር አገልግሎት መስጠት
  • የሠራተኞችን መረጃ ማጠናቀር፤ለተገቢው አካል ማስተላለፍ
  • በጡረታ የሚሰናበቱትን በመለየት ማሳወቅ፤ቅጽ መሙላት ለማህበራዊ ዋስትና ማስተላለፍ
  • በመ/ቤቱ አመራር(management) ውስጥ የሥራ ሂደቱን በመወከል መሥራት

በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት

  1. አንድ የሥራ ሂደቱ ባለቤት
 
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-
  • የሠው ሃብት ልማት የሥልጠና ፍላጎት ማጥናት
  • የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ክፍተት መለየት
  • የሰው ሃብት ልማት የአሰራር ችግርን ማጥናት
  • ዕጩ ሰልጣኞችን መመልመል
  • የሥልጠና ሞጁል ማዘጋጀት
  • ሥልጠና መስጠት
  • ሥልጠና ያመጣውን ፋይዳ መገምገምና ለቀጣይ ሥልጠና ማሻሻያ ማድረግ
  • የውጭ ሃገር ትም/ትና ሥልጠና ዕድሎችን ማስተባበር
  • ተግባራትን ማቀድ፤መከታተል፤መገምገምና ሪፖርት ማቅረብ እንዲሁም ግብረ-መልስ መስጠት

በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት

  1. አንድ የሥራ ሂደቱ ባለቤት
 
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-
  • እንደ ግብርና ፤ ጤናና ትምህርት ለመሳሰሉት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች በኮምፒውተር የታገዘ መረጃ እንዲኖራቸው ኔትወርክ መዘርጋት
  • በመንግስት ተቋማት ያሉ መረጃዎች ዳታ ቤዝ ማቋቋም፤የመረጃ ቋትና ድህረ ገጽ) ተደራጅተውና ተቀናጅተው ሥራ ላይ የሚውሉበት ሥርዓት መዘርጋት
  • የቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ ማዕከል ማቋቋምና አገልግሎት መስጠት
  • የማህበረሰብ የመረጃ ማዕከላትን ማቋቋም(ኮሙኒቲሬዲዮ፤ቴሌሴንተር፤ኮምፒውተር ሴንተር)
  • በኢኮቴ ዘርፍ የሰው ኃይል ሥልጠናና የምክር አገልግሎት መስጠት
  • የገጠሩን ህብረተሰብ መሰረታዊ የመረጃ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ(Rural connectivity)
  • የሴቶችና አካል ጉዳተኞች የሚያጎለብት መሰረታዊ የመረጃ ሥርዓቶችና ፕሮግራሞች መደገፍ
  • የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና ማድረግ

በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት

1.የሥራ ሂደቱ አስተባባሪ
1.1. የኔትዎርክ ስልጠና ባለሙያ
1.2.የጥገና፤የቪዲዮኮንፍረንስ ና ዳታ ባለሙያ

 
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-
  • የልማት ዕቅዶችን /መካከለኛ፤የአምስት ዓመትና ዓመታዊ/ማዘጋጀት
  • ዓመታዊ በጀትና የድረጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት
  • የአፈጻጸም ክትትል ሪፖርት/በ3፤በ6፤በ9ና በዓመት/ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ
  • የመያድ ፕሮጄክቶችን ክትትልና ግምገማ ማድረግ
  • የሴክተሩን ዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ከሴክተሩ ዓላማና ራዕይ እንዲሁም ግብ በመነሳት መተንተንና በመረጃነት ማጠናቀር
  • የመምሪያውን ተግባራት በማሰባሰብ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ መረጃ መሥጠት
  • በግልና በጋራ የሚሰጡ ተግባራትን መወጣት
 
 
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡-
  • የዞንና ወረዳ አቅም ግንባታ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ያሰራጫል
  • የመረጃ ምንጭ በመሆን ያገለግላል
  • የመረጃ ሥርዓትን ለማጠናከር ያጠናል፤አፈጻጸማቸውን ይከታታላል፣ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል
  • የሴክተር መ/ቤቶች የልማትና ሌሎች መረጃዎችን እንዲያሰባስቡና አደራጅተው እንዲይዙ ምክር ይሰጣል፣የመረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ዘዴን ይቀይሳል፤
  • በየእርከኑ የሚገኙ ጽ/ቤቶች የሚያደርጉትን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደግፋል፣ይከታታላል፣ ይገመግማል ፤ድጋፍ ይሰጣል፡፡
 
Copyright © Dawero Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Dawero Zone Capacity Building Website