በገጠር ወረዳና ቀበሌ አቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ፓኬጅ አፈጻጸም በተመለከተ የፌዴራል አቅም ግንባታ ሚኒስቴር ባለሙዎች በክልሉ ብሎም በዞኑ በተመረጡ የማረቃ ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች በመገኘት የሥራ ግምገማ ማድረጋቸው ተዘገበ፡፡
በማረቃ ወረዳ በሚገኙ ሶስት ቀበሌዎች ማለትም በከፍተኛ አፈጻጸም የመዳኩይሊ ቀበሌ፣በመካከለኛ አፈጻጸም የኢየሱስ ቀበሌና በዝቅተኛ አፈጻጸም የአሩሲ ቀበሌዎች እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡
ቡድኑ በቀበሌው የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞችን የቀበሌ ካቢኔ አባላትን የወጣትና ሴቶች ሊግ አባላትንና ታዋቂ ግለሰቦችን በቁጥር 30 በተዘጋጀ ቼክሊስት መሰረት የመልካም አሰተዳደር ፓኬጅ አፈጻጸምን በተመለከተ ግምገማ ያደረገ ሲሆን በየቀበሌዎቹ በሰፈረው አስተያየት እንደተመለከተው ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማጎልበት ሊሻሻሉ የሚገባቸውንም በመለየት ለቀጣይ ትግበራ መዘጋጀት እንደሚገባ መግለጻቸውን ከሥፍራው የደረሰን ሪፖርት አመልክቷል፡፡ |