መጋቢት 30/2001ዓም>>>
በኢሰራ፣ በማረቃና ቶጫ ወረዳዎች ባለፉት ወራት የመሰረታዊ የሥራ ሂደት አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በቀጣዩ ለውጡን ለመምራት ምን ይጠበቃል በሚል ርዕስ ውይይትና የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች ሠራተኞች የተሳተፉና ሁሉም በወረዳ አስተዳዳሪዎችና የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት ሲሆን በየመድረኩም ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢው መልስ የተሰጣቸው እንደነበረ ታውቋል፡፡ውይይቱ በአብዛኛው በብዙዎች ዘንድ የነበረውን ብዥታ ያጠራና ለለውጥ ያዘጋጀ ከመሆኑም በላይ ሲቪል ሰርቪሱ በትጋትና በብቃት አገልግሎት አሰጣጡን እንዲያሻሽል የሚረዳው እንደሆነ በሥፍራው የተገኙት ዘጋቢዎቻችን አስታውቀዋል፡፡