የካቲት 24-25/2001ዓም>>>
በዞናችን የተጀመረውን አበረታች በምግብ ራስን የመቻልና ለሌሎች የመትረፍ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የሚረዳ በተፋሰስ ልማት ላይ ያተኮረ ስልጠና በሎማ ወረዳ አቅም ግንባታና በወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤቶች ትብብር መሰጠቱ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል፡፡ በወረዳው ለሚገኙ 58 የግብርና ልማት ሠራተኞች የተሰጠው ይህ ስልጠና በቪዲዮ የተደገፈና ለተጀመረው ልማት ሁለገብ ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነ በተሳታፊዎች መገለጹ ተመልክቷል፡፡ የሎማ ወረዳ የኢኮቴ የሥራ ሂደት ካሁን ቀደምም በየሴክተሩ የሚገኙ ኮምፒውተሮችን በማሰባበሰብ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና መስጠቱም ሣይጠቀስ የማይታለፍ እንደሆነም ዘጋቢያችን አስታውሷል፡፡