e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Thursday, November 26, 2009 4:15 PM
 
note

ግንቦት 3/2001ዓም>>>

 new የአፈጻጸም ውል ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡

headline በዳውሮ ዞን በሚገኙ ሰባት ሴክተሮች እየተተገበረ የሚገኘውን መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራ አፈጻጸም ለመደገፍ ከመምሪያችን የለውጥ ፕሮ/ፕሮ/ጥናትና ትግበራ ዋና የሥራ ሂደትና

የየሴክተሩ ኃላፊዎች የክትትልና ግምገማ ድጋፍ ውል ስምምነት ሰነድ ተፈረመ፡፡
ሰባቱ ሴክተሮች በትግበራው ወቅት የሚያሳዩዋቸውን እመርታዎች እየመዘገበ በግብዓትነት በመጠቀም ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ደግሞ ድጋፍ በማድረግ ለውጡን የተሳካ ማድረግ የሥራ ሂደቱ ዋና ተልዕኮ እንደሆነና በዚህም መነሻነት ለውጡ እማይቀለበስበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ በየሳምንቱ በየሴክተሩ በመገኘት ድጋፋዊ ክትትሉ የሚቀጥል እንደሆነም ከሥራ ሂደቱ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ካሁን ቀደምም ለሶስት ተከታታይ ዙሮች በየሴክተሩ ድጋፋዊ ክትትል ተደርጎ ግብረ-መልስ የተሰጠ ሲሆን ከስምምነት ውሉም በተጨማሪ በተቀሩት ስምንት ሴክተሮች የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴው ምን እንደሚመስል ለማወቅ ቼክ ሊስት የተዘጋጀና ተግባራዊ እንቅስቃሴውም የተጀመረ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 . . . Next>>
Copyright © Dawero Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Dawero Zone Capacity Building Website