e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Zonal Civil Service Departments
6th Woredas and 2 town administrations
Dilla University
Gedeo Development Associations
Our Customers
Last Updated Thursday, February 11, 2010 3:38 PM
 
note
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በሀገራችን ኢትዮጽያ በዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየውን ድህነትና |ላቀርነት ለማስወገድ የልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስትራቴጂ ሀገራችን መሀከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተነደፈውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል በመሆኑ ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ የመንግስት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችና ተግባራዊነትም ለልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጠናከር ጉልህ ድርሻ ስላላቸው ስትራቴጂውን ለማሳካት የተለያዩ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተነድፈው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረጉ ከዚህ ቀደም በሲቪል ሰርቪስ የነበረው የተገልጋይነት ስሜት እየተቀነሰ የአገልጋይነት ስሜት እየዳበረ ዛሬ ተገልጋዮች በመንግስት መ/ቤቶች ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋነት ህብረተሰቡ ለልማቱና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያሳድግ አድርጕል፡፡ በሲቪል ሰርቪሱም ዛሬ የሚታየው በቅልጥፍና ሥራ ላይ የሚታየው ጥረት በውጤት ካልተደገፈ በስተቀር ሀገራዊ ራዕይ በተፈለገው ጊዜ እውን ሊሆን ስለማይቻል እያንዳንዱ ተግባር በቅልጥፍናና በውጤታማነት እየተመዘነ መከናወን ስላለበት የሥራ አፈጻጸም ምዘናና ሥርዓት ተዘርግቶ እያንዳንዱ ፈጻሚ አካል ባስመዘገበው ውጤት መሠረት ሊመሰገንና ሊወቀስ የሚቻልበት አሠራር ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ የእያንዳንዱ ተግባር ቅልጥፍናና ውጤታማነት እየተመዘነ እንዲሄድ ማድረግ የተነደፉት የልማት ግቦች በተፈለገው ጊዜ ተሳክቶ ህብረተሰቡ የልማቱ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑ የህብረተሰቡ የልማቱ ተጠቃሚነት የሀገራችንን እድገትና ማሻሻል የሚያሳይ በመሆኑ የቅልጥፍናና የውጤታማነት መመጋገብ ከሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አካôያ ሁሉም ፈጻሚ በተሰማራበት የሥራ መስክ የሚፈልገውን ውጤት በተፈለገው ጊዜና ወጪ የማስመዝገብ ጉዳይ የዜግነት ግዴታ ሊሆን ይገባል፡፡ በየሴክተሩ ያለው በጎ ጅምር የበለጠ ለማጠናከር ቀልጣፋና ውጤታማ አፈጻጸም ለማጎልበት በሁሉም የመንግስት መ/ቤቶች እየተተገበረ ያለው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) በሲቪል ሰርቪስና በህብረተሰቡ መሀከል የሚኖረውን ግንኙነት ጤናማ ከማድረጉም ባሻገር ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ የሚኖረውን እምነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለ BPRትግበራየሁሉንምፈጻሚትኩረትየሚሻይሆናል፡፡ አቅም ግንባታ ሴክተር የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ፣ የመልካም አስተዳደር ፓኬጅና በፍትህ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወኑ ተግባሮች በመሆናቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ፕሮግራሞችን በማስፋጸምና ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በበለጠ የማስፋት ሥራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡


 
 
 
Copyright © Gedieo Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Gedieo Zone Capacity Building Website