e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Thursday, February 11, 2010 3:36 PM
note
 
Department Head

በሀገራችን ኢትዮጽያ በዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየውን ድህነትና |ላቀርነት ለማስወገድ የልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስትራቴጂ ሀገራችን መሀከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተነደፈውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል በመሆኑ ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ የመንግስት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችና ተግባራዊነትም ለልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መጠናከር ጉልህ ድርሻ ስላላቸው ስትራቴጂውን ለማሳካት የተለያዩ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተነድፈው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረጉ ከዚህ ቀደም በሲቪል ሰርቪስ የነበረው የተገልጋይነት ስሜት እየተቀነሰ የአገልጋይነት ስሜት እየዳበረ ዛሬ ተገልጋዮች በመንግስት መ/ቤቶች ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋነት ህብረተሰቡ ለልማቱና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንዲያሳድግ አድርገôል፡፡ በሲቪል ሰርቪሱም ዛሬ የሚታየው በቅልጥፍና ሥራ ላይ የሚታየው ጥረት በውጤት ካልተደገፈ በስተቀር ሀገራዊ ራዕይ በተፈለገው ጊዜ እውን ሊሆን ስለማይቻል እያንዳንዱ ተግባር በቅልጥፍናና በውጤታማነት እየተመዘነ መከናወን ስላለበት የሥራ አፈጻጸም ምዘናና ሥርዓት ተዘርግቶ እያንዳንዱ ፈጻሚ አካል ባስመዘገበው ውጤት መሠረት ሊመሰገንና ሊወቀስ የሚቻልበት አሠራር ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ የእያንዳንዱ ተግባር ቅልጥፍናና ውጤታማነት እየተመዘነ እንዲሄድ ማድረግ የተነደፉት የልማት ግቦች በተፈለገው ጊዜ ተሳክቶ ህብረተሰቡ የልማቱ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑ የህብረተሰቡ የልማቱ ተጠቃሚነት የሀገራችንን እድገትና ማሻሻል የሚያሳይ በመሆኑ የቅልጥፍናና የውጤታማነት መመጋገብ ከሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አካôያ ሁሉም ፈጻሚ በተሰማራበት የሥራ መስክ የሚፈልገውን ውጤት በተፈለገው ጊዜና ወጪ የማስመዝገብ ጉዳይ የዜግነት ግዴታ ሊሆን ይገባል፡፡ ..... ተጨማሪ>>

 
note

ጥር10 2002ዓም>>>

 new በጌዴኦ ዞን የሲቪል ሰርቪሱ የአገልግሎት ስሜት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

headline ይህ የተገለጸው የጌዴኦ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ በጥር 10/2002 የሴክተሩን የ2002 ዕቅድ አፈጻጸም ከወረዳና ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኑበት ግምገማ በተደረገበት ወቅት በ2002 የክልሉ መንግስት ሠራተኞች በመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡና በሀገራችን መብግስት ልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ለመገንባት ከሲቪል ሰርቪሱ ሚና ምን መሆን እንዳለበት በጠሰጠው ስልጠና በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ በአገልጋይነትና በቡድን ስሜት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ ተግባር ለመፈጸ፣ ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ..... ተጨማሪ>>

 
News....Start from the Latest <<Prev 1..... Next>>
የጌዴኦ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ
የመምሪያው አድራሻ
ስልክ ፡- +251-46-3312115
ፖስታ፡- 6
ፋክስ፡- +251-46-2200072

ኢሜይል፡-gedeozone_capbui@ymail.com

ዲላ፣ኢትዮጵያ
Copyright © Gedieo Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Gedieo Zone Capacity Building Website