e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Wednesday, December 9, 2009 7:59 PM
“ ምንጊዜም ለወርቅ እንሠራለን!!! ”
note
 
Department Head

ዞናችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልማቱም ህዝቡን በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም የመገንባት ስራ ትኩረት በመስጠት መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) በሁሉም የመንግስት ተቋማት ተቋማዊ ለውጥና መሠረት እንዲይዝ ከፍተኛ ትኩረት መሠጠት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት በዞናችን ወደ መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ትግበራ በገቡትም ሆነ በቅርቡ ጥናታቸው ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ ለሚገቡት ሴክተሮች የማስተላልፈው መልዕክት አሁን ካለንበት የዕድገት ደረጃ አሁን ዓለም ወደ ደረሰበት ደረጃ ለመድረስ አቋራጩና ብቸኛው መንገድ መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ መሂኑ በጥናትም የተረጋገጠ ሀቅ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁላችንም በአንድነት መረባረብና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በአንድነት በመስራት ለመወጣት በዞናችን በአቅም ግንባታና በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት እየተካሄደ ባለው መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሠረት ስራችን በማከናወንአዳዲስ አስተሳሰቦችንና አሠራሮችን በመፍጠር አሁን ካለበት ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ ጠንክረን እንሰራለን፡፡...ተጨማሪ>>

 
note

መስከረም 7 2002ዓም>>>

 new ከመስከረም 5-7/2002 ዓ/ም ድረስ የአቅም ግንባታ ሴክተር የምክክር ጉባዔ ተካሄደ፡፡

headline ከመስከረም 5-7/2002 ዓ/ም ድረስ የአቅም ግንባታ ሴክተር የምክክር ጉባዔ ተካሄደ፡፡ ጉባዔው የዞን መምሪያዎች ኃላፊዎችን፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የወረዳ የለውጥ ፕ/ፕ/ጥ/ት/ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የወረዳ የልማት ዕቅድ ዝ/ክ/ግ/ግ/ የስራ ሂደት ፈጻሚዎች፣ የወረዳ የፍትህና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የወረዳ የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊዎችና የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ በጉባዔውም ላይ አጠቃላይ የ2001 ዓ/ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት፣ የ2002 ጠቋሚ ዕቅድ፣ ኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ እና ከወረዳዎች ጋር የግብስምምነት ፊርማን ያካተተ ጉባዔ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡ ..... ተጨማሪ>>

 
ሰኔ 2001ዓም>>>

new የየተቋማቱን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች በወር 1 ቀን በመገኘት የተሞክሮ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

headline መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጡን እንደ ስርዓት አድርጎ በየተቋማቱ ለመትከል የየተቋማቱን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች በአቅም ግንባታ ሴክተር ሰብሳቢነት በወር 1 ቀን በመገኘት የተሞክሮ ልውውጥ በማድረግ መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጡ ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው መሠረት መጣሉን መምሪያው አስታወቀ፡፡ ..... ተጨማሪ>>
 
ሰኔ 19 2001ዓም>>>
new መሠረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀት ስልጠና ከዞኑ 9 ሴክተር መ/ቤቶች ለተውጣጡ 25 ባለሙያዎች መሠጠቱን የዞኑ መምሪያ አስታውቋል፡፡
headline በበጀት ዓመቱ መጋቢት 6 እስከ ሰኔ 19/2001 ዓ/ም በኢኮቴ መሠረተ ልማት ማስፋፋትና በዘርፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት መሠረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀት ስልጠና ከዞኑ 9 ሴክተር መ/ቤቶች ለተውጣጡ 25 ባለሙያዎች መሠጠቱን የዞኑ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ... ተጨማሪ>>
 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 6 7 . Next>>
የጋሞ ጎፋ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ
የመምሪያው አድራሻ
ስልክ ፡- +251-46-8810152
ፖስታ፡- 157
ፋክስ፡- +251-46-8810618
ኢሜይል፡- ggzbc@ethionet.et
አርባ ምንጭ ፣ኢትዮጵያ
Copyright © Gamo Gofa Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Gamo gofa Zone Capacity Building Website