ሰኔ 2001ዓም>>>
መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጡን እንደ ስርዓት አድርጎ በየተቋማቱ ለመትከል የየተቋማቱን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች በአቅም ግንባታ ሴክተር ሰብሳቢነት በወር 1 ቀን በመገኘት የተሞክሮ ልውውጥ በማድረግ መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጡ ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው መሠረት መጣሉን መምሪያው አስታወቀ፡፡ በዚህም መሠረት በዞኑ ጥናቱ በተጠናቀቀባቸው ሴክተሮች አፈጻጸም መሠረት ጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ የአቅም ግንባታ መምሪያ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ፣ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ፣ አርባምንጭ ማረሚያ ቤት፣ የተሸለ አፈጻጸም ያሳዩ መሆናቸውን መምሪያው ገልጿል፡፡