ሰኔ 19 2001ዓም>>>
በበጀት ዓመቱ መጋቢት 6 እስከ ሰኔ 19/2001 ዓ/ም በኢኮቴ መሠረተ ልማት ማስፋፋትና በዘርፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት መሠረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀት ስልጠና ከዞኑ 9 ሴክተር መ/ቤቶች ለተውጣጡ 25 ባለሙያዎች መሠጠቱን የዞኑ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ስልጠናው የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ፣ የማይክሮሶፍት ኦፊስ እና የኢንተርኔት አጠቃቀምን ያካተተና ለ60 ሰዓታት የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡