
|
 |
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡- |
- የአፈጻጸም ከፍተትን መለየት፤
- ጥናት እንዲካሄድና የማስፈጸም ሰነድ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
- በፓይለት የተፈተሸ የማስፈጸሚያ ሰነድ መረከብ፤
- የትግበራ ዕቅድ ማዘጋጀትና ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤
- የትግበራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- የፋይዳ ግምገማ ማድረግ፤
- የጥናት ሥራውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራሞችንና የሪፎርም ተግባራትን ይመራል፤ይደግፋል፤ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤
በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት
- የሥራ ሂደቱ አስተባባሪና የፕሮጄክት ዕቅድ ክትትል ግምገማ ባለሙያ(2)
|
| |
|
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡- |
- ተጠንተው የተወሰኑ የሥራ ደረጃና ጥቅማ ጥቅሞችን በመስፈርቱ መሰረት ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ
- የሠው ሃብት ፍላጎትና ዕቅድ ማዘጋጀት
- በቅጥር ፤በዝውውር እና በደረጃ እድገት የሰው ሃብት ማሟላት፤መመዝገብ
- ፈቃድ በፕሮግራሙ መሰረት መፈጸሙን ማረጋገጥ
- የሥራ ሂደቶችን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ውጤቶችን ማሰባሰብ፤ማደራጀትና ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ
- የዲስፕሊን ርምጃ መውሰድ
- የድጋፍ ፤የክትትልና ምክር አገልግሎት መስጠት
- የሠራተኞችን መረጃ ማጠናቀር፤ለተገቢው አካል ማስተላለፍ
- በጡረታ የሚሰናበቱትን በመለየት ማሳወቅ፤ቅጽ መሙላት ለማህበራዊ ዋስትና ማስተላለፍ
- በመ/ቤቱ አመራር(management) ውስጥ የሥራ ሂደቱን በመወከል መሥራት
በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት
- አንድ የሥራ ሂደቱ ባለቤት
|
| |
|
| የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡- |
- የሠው ሃብት ልማት የሥልጠና ፍላጎት ማጥናት
- የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ክፍተት መለየት
- የሰው ሃብት ልማት የአሰራር ችግርን ማጥናት
- ዕጩ ሰልጣኞችን መመልመል
- የሥልጠና ሞጁል ማዘጋጀት
- ሥልጠና መስጠት
- ሥልጠና ያመጣውን ፋይዳ መገምገምና ለቀጣይ ሥልጠና ማሻሻያ ማድረግ
- የውጭ ሃገር ትም/ትና ሥልጠና ዕድሎችን ማስተባበር
- ተግባራትን ማቀድ፤መከታተል፤መገምገምና ሪፖርት ማቅረብ እንዲሁም ግብረ-መልስ መስጠት
በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት
- አንድ የሥራ ሂደቱ ባለቤት
|
| |
|
| የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡- |
- እንደ ግብርና ፤ ጤናና ትምህርት ለመሳሰሉት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች በኮምፒውተር የታገዘ መረጃ እንዲኖራቸው ኔትወርክ መዘርጋት
- በመንግስት ተቋማት ያሉ መረጃዎች ዳታ ቤዝ ማቋቋም፤የመረጃ ቋትና ድህረ ገጽ) ተደራጅተውና ተቀናጅተው ሥራ ላይ የሚውሉበት ሥርዓት መዘርጋት
- የቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ ማዕከል ማቋቋምና አገልግሎት መስጠት
- የማህበረሰብ የመረጃ ማዕከላትን ማቋቋም(ኮሙኒቲሬዲዮ፤ቴሌሴንተር፤ኮምፒውተር ሴንተር)
- በኢኮቴ ዘርፍ የሰው ኃይል ሥልጠናና የምክር አገልግሎት መስጠት
- የገጠሩን ህብረተሰብ መሰረታዊ የመረጃ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ(Rural connectivity)
- የሴቶችና አካል ጉዳተኞች የሚያጎለብት መሰረታዊ የመረጃ ሥርዓቶችና ፕሮግራሞች መደገፍ
- የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና ማድረግ
በዞን የሚገኝ የሰው ሃብት
1.የሥራ ሂደቱ አስተባባሪ
1.1. የኔትዎርክ ስልጠና ባለሙያ
1.2.የጥገና፤የቪዲዮኮንፍረንስ ና ዳታ ባለሙያ
|
| |
|
| |
| የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት፡- |
- የዞንና ወረዳ አቅም ግንባታ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ያሰራጫል
- የመረጃ ምንጭ በመሆን ያገለግላል
- የመረጃ ሥርዓትን ለማጠናከር ያጠናል፤አፈጻጸማቸውን ይከታታላል፣ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል
- የሴክተር መ/ቤቶች የልማትና ሌሎች መረጃዎችን እንዲያሰባስቡና አደራጅተው እንዲይዙ ምክር ይሰጣል፣የመረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ዘዴን ይቀይሳል፤
- በየእርከኑ የሚገኙ ጽ/ቤቶች የሚያደርጉትን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደግፋል፣ይከታታላል፣ ይገመግማል ፤ድጋፍ ይሰጣል፡፡
|
|
| |
|
  |