|
| |
|
Last Updated
Wednesday, December 30, 2009 11:32 PM
  |
| |
    |
| |
|
በዞናችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልማቱም ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ወሣኝ ነው ፡፡ ስለሆነም የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራን በአዲስ አሰራር አደረጃጀትና በበቃ የሠው ሀይል ልማትና አሠራር በመታገዝ፣ በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማገዝና በማቀላጠፍ ተቋማዊ ለውጥ እውን ማድረግና መልካም አስተዳደር እመርታ ማምጣት እንዲያስችል የሴክተሩ የሥራ ሂደቶች የጋራ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ፡፡በመሆኑም በየደረጃው የሚታዩትን የማስፈፀም አቅም ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ፈጥኖ ስልት በመቀየስ በተግባር ላይ እንዲውል በማድረግና የሪፎርም ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል ፡፡ በአጠቃላይ የመምሪያው የሥራ ሂደቶች በዋናነት የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ስርዓት ማስፈን፣ በመንግስት ተቋማት ቀልጣፋና ውጤታማ አሠራርን መሠረት ያደረገ ስራ ሊሠሩ ይገባል ፡፡ በዚህ መሠረት የአቅም ግንባታ ሴክተር ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራትንና ያጋጠሙትን ችግሮች በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር ሀገሪቷ እያከናወነች ላለችው የልማት እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
|
|
| |
|
  |
|
|