e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Last Updated Wednesday, December 30, 2009 11:25 PM
note
 
Department Head

በዞናችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልማቱም ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ወሣኝ ነው ፡፡ ስለሆነም የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራን በአዲስ አሰራር አደረጃጀትና በበቃ የሠው ሀይል ልማትና አሠራር በመታገዝ፣ በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማገዝና በማቀላጠፍ ተቋማዊ ለውጥ እውን ማድረግና መልካም አስተዳደር እመርታ ማምጣት እንዲያስችል የሴክተሩ የሥራ ሂደቶች የጋራ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ፡፡በመሆኑም በየደረጃው የሚታዩትን የማስፈፀም አቅም ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ፈጥኖ ስልት በመቀየስ በተግባር ላይ እንዲውል በማድረግና የሪፎርም ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል ፡፡ በአጠቃላይ የመምሪያው የሥራ ሂደቶች በዋናነት የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ስርዓት ማስፈን፣ በመንግስት ተቋማት ቀልጣፋና ውጤታማ አሠራርን መሠረት ያደረገ ስራ ሊሠሩ ይገባል ፡፡ በዚህ መሠረት የአቅም ግንባታ ሴክተር ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራትንና ያጋጠሙትን ችግሮች በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር ሀገሪቷ እያከናወነች ላለችው የልማት እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማድረግ ይኖርበታል፡፡... ተጨማሪ>>

 
note

መስከረም 2002ዓም>>>

 new በየወረዳው ለሚገኙ ሠራተኞች መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ገለፀ ::

headlineየጉራጌ ዞን የኢኮቴ መሠረተ ልማት አቅርቦትና አገልግሎት የሥራ ሂደት ከኢንቴል የኮምፒዩተር ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር በመተባበር በየወረዳው ለሚገኙ ሠራተኞች መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ገለፀ :: የስራ ሂደቱ አስተባበሪ የሆኑት አቶ መቻል አንዴ እንደገለፁት ሠራተኞቹን ስልጠና መስጠት ያስፈለገው አዲሱ መሠረታዊ የአሰራር ለውጥ በሚያዘው መሰረት ሠራተኞች ሥራቸውን ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ ዘዴያቸውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡፡ ..... ተጨማሪ>>

 
ሐምሌ 2001ዓም>>>

new የዞን አቅም ግንባታ መምሪያ በ 2001 ዓ.ም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን በዞኑ ባሉ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች ለመቅጠር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ ::

headline የጉራጌ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ በ 2001 ዓ.ም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን በዞኑ ባሉ 13 ወረዳና 2 ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች ለመቅጠር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ..... ተጨማሪ>>
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 . . . ..... Next>>
የጉራጌ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ
የመምሪያው አድራሻ
ስልክ ፡- +251-11-3300116
ፖስታ፡- 202
ፋክስ፡- +251-11-3301337
ኢሜይል፡-guragiecapacity@yahoo.com
ወልቂጤ፣ኢትዮጵያ
Copyright © Gurage Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Gurage Zone Capacity Building Website