
በዞናችን ፈጣን ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልመቱ በላቀ ደረጃ ተጠቀሚ የሚሆንበት ሥርዓት ለመዘርጋትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና አላቸዉ፡፡
በመሆኑም የዞናቸን ህዝቦች ሁሉ ካሉበት ድህነትና ኃለቀርነት እንዲላቀቅ በቀደሙት ዓመታት እየተመዘገቡ ያሉ የልማትና አስተዳደር ወጤቶች ዘላቂ እንደሆኑ ብሎም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርሱ በዞኑ ዉስጥ ባሉ የሚታዩ የማስፈጸም አቅም ችግሮችን(ማነቆዎችን) ለመፍታት ትኩረት አድርገን እንሰራለን፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ዋነኛዉ መሰረታችን በመሰረታዊ አሠራር ለዉጥ ጥናት ዉጤቶችን መሠረት በማድረግ አደረጃጀትና አሰራር የሚሰሩ ስራዎች ላይ ማለትም የአቅም ግንበታ ፕሮግራሞችን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን፡፡ የተንዛዛ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የጎደለዉን እንዲሁም ድግግሞሽ የበዛበትን የስልጠናና ትምህርት ሥርዓቶች ለዉጦ በምትኩ ፍላጎትንና ክፍተትን መሰረት ያደረገ ሥርዓት ለማስፈን በየደረጃዉ የሚካሄዱ ማህበራዊ ፡ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የለዎጥ ስራዎች ዉስጥ በብቃት የሚሳተፍ ሲቪል ሰርቫነት ለመፍጠር ነዉ፡፡ ደግሞም ኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ በዞኑ ዉስጥ እንዲስፋፋና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፈጠን ሆነ እንደ አንድ ኢንዱስትሪ ለማጎልበት የራሱን የልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ሆኖ ኢኮቴ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ላልተማከለ አስተዳደር ማጎልበት የድርሻዉን እንዲወጣ እናደርጋለን፡፡