በዞናችን ፈጣን ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ከልመቱ በላቀ ደረጃ ተጠቀሚ የሚሆንበት ሥርዓት ለመዘርጋትና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች ወሳኝ ሚና አላቸዉ፡፡ በመሆኑም የዞናቸን ህዝቦች ሁሉ ካሉበት ድህነትና ኃለቀርነት እንዲላቀቅ በቀደሙት ዓመታት እየተመዘገቡ ያሉ የልማትና አስተዳደር ወጤቶች ዘላቂ እንደሆኑ ብሎም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርሱ በዞኑ ዉስጥ ባሉ የሚታዩ የማስፈጸም አቅም ችግሮችን(ማነቆዎችን) ለመፍታት ትኩረት አድርገን እንሰራለን፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ዋነኛዉ መሰረታችን በመሰረታዊ አሠራር ለዉጥ ጥናት ዉጤቶችን መሠረት በማድረግ አደረጃጀትና አሰራር የሚሰሩ ስራዎች ላይ ማለትም የአቅም ግንበታ ፕሮግራሞችን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን፡፡ .... ተጨማሪ>>
ጥር 13 2002ዓም>>>
የሀዲያ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በማስፋፋት ለህዝቡ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ቀደም ሲል በከንቲባዉ ጽ/ቤት ማለትም በሀዲያ ዞን አሰተዳደር ቅጥር ግቢ ዉስጥ የነበረዉና ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጥ የነበረዉ ይህ የአገልገሎት ማዕከል ለህዝቡ በተሻለ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆንና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ በማለት ወደ ዞኑ አቅም ግንበታ ግቢ በማዛወር ለህብረተሰቡ የኮምፕዩተር ስልጠና'የኢንተርኔትና ነጻ የልምምድ አገልገሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከል 12 ዴስከቶፕ ኮምፕዩተሮች ያሉት ሲሆን፤ በኢኮቴ የስራ ሂደት አሰተባባሪነት የCDMA ኔትወርኪንግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉንም ኮምፕዩተሮች በሲሰኮ ስዊቺንግ በማገናኘት ሁሉም ኮምፕዩተሮች ተመጣጣኝ ፍጥነት እነዲኖራቸዉ በማድረግ ጥሩ የሚባል የኢንተርኔት አገልገሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሌላዉ በዚህ ማዕከል የሚሰጠዉ አገልግሎት የመሰረታዊ ኮምፕዩተር ስልጠና ሲሆን ይህም ስልጠና በኢኮቴ የስራ ሂደት የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑም ጊዜ የመጀመሪያዉን ስልጠኛ ጨርሶ ለሁለተኛ ጊዜ ከዞኑ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሰልጣኞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፤ስልጠናዉ የሚሰጠበት ሰዓት የስራ ሰዓትን እንዳይሻማ በማሰብ ከስራ ሰዓት ዉጪ ነዉ፡፡ባጠቃላይ ይህ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ህብረተሰቡ ለኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ ጥሩ ግንዛቤ አንዲኖረዉና ለመረጃ ቅርብ እንዲሆን ጥሩ የሆነ አሰተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህን አገልግሎት የበለጠ ለመሳደግና ህብረተሰቡን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመድረግ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡..... ተጨማሪ>>