ጥር 13 2002ዓም>>>
የሀዲያ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በማስፋፋት ለህዝቡ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ቀደም ሲል በከንቲባዉ ጽ/ቤት ማለትም በሀዲያ ዞን አሰተዳደር ቅጥር ግቢ ዉስጥ የነበረዉና ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጥ የነበረዉ ይህ የአገልገሎት ማዕከል ለህዝቡ በተሻለ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆንና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ በማለት ወደ ዞኑ አቅም ግንበታ ግቢ በማዛወር ለህብረተሰቡ የኮምፕዩተር ስልጠና'የኢንተርኔትና ነጻ የልምምድ አገልገሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከል 12 ዴስከቶፕ ኮምፕዩተሮች ያሉት ሲሆን፤ በኢኮቴ የስራ ሂደት አሰተባባሪነት የCDMA ኔትወርኪንግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉንም ኮምፕዩተሮች በሲሰኮ ስዊቺንግ በማገናኘት ሁሉም ኮምፕዩተሮች ተመጣጣኝ ፍጥነት እነዲኖራቸዉ በማድረግ ጥሩ የሚባል የኢንተርኔት አገልገሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሌላዉ በዚህ ማዕከል የሚሰጠዉ አገልግሎት የመሰረታዊ ኮምፕዩተር ስልጠና ሲሆን ይህም ስልጠና በኢኮቴ የስራ ሂደት የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑም ጊዜ የመጀመሪያዉን ስልጠኛ ጨርሶ ለሁለተኛ ጊዜ ከዞኑ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሰልጣኞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፤ስልጠናዉ የሚሰጠበት ሰዓት የስራ ሰዓትን እንዳይሻማ በማሰብ ከስራ ሰዓት ዉጪ ነዉ፡፡ባጠቃላይ ይህ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ህብረተሰቡ ለኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ ጥሩ ግንዛቤ አንዲኖረዉና ለመረጃ ቅርብ እንዲሆን ጥሩ የሆነ አሰተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህን አገልግሎት የበለጠ ለመሳደግና ህብረተሰቡን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመድረግ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡