የዞኑ አቅም ግንባታ መምሪያ የ 2001 ዓመታዊ ጉባኤ ከ ጥቅምት 26 እስከ 27 2002 ዓ.ም የወረዳ አቅም ግንባታ ሴክተር ኃላፊዎች በተገኙበት ለ ሁለት ቀናት ተካሂዷል። በጉባኤዉ ላይ የዞኑ ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን 10ሩም ወረዳዎች የየራሳቸዉን ዓመታዊ ሪፖርት ማቅረባቸዉ ታዉቋል። በዚሁጉባኤ በተሰብሳቢዎች የቀረቡት ዋና ዋና ጉዳቶች
- መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ ለማጠናከር ከፍተኛ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እጥረት
- የልዩ ልዩ መሥሪያ መሳሪያዎች እጥረት
- የበጀት አነስተኛ መሆን በትኩረት ለጉባኤዉ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል
በሌላ በኩል የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ ለማጠናከር ከተያዙት የህዝብ ግኑኝነት ሥራ ረገድ በዞኑ በቅርብ በሙከራ ስርጭት ላይ ባለዉ ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4 በሦስት የተለያዩ ጊዜያት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ማለት ምን እንደሆነና ይኸንኑ በመተግበር ላይ ያሉት ሴክተር መ/ቤቶች እያከናወኑ በተጨባጭም ያመጡት ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን የተነተነ መግለጫ በመምሪያ ኃላፊ ተሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪም የ2001 የአቅም ግንባታ ሴክተር ዓመታዊ ጉባኤ በኤፍ ኤም 97.4 ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶታል። ከዚህ ሌላ የ 2002 ግማሽ ዓመት የአቅም ግንባታ በልዩ ሁኔታ ወረዳዎች በጥልቀት በገመገመ ሪፖርት መነሻነት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። |