መምሪያችን የሚሊኒየም ግቦችን ለማሳካት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በአገራችን ድህነት ታሪክ ሆኖ እንዲቀር የሚሊኒየም ግቦችን በማሳካት ከሁለት አስርት አመታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አገሪቷ ከድህነት ወለል በላይ ሆና በመካከለኛ ደረጃ በደረሱ ሀገሮች ተራ እንድትሰለፍ ሁሉም የልማት አቅሞችን በተቀላጠፈና ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማስቻልን ያለመ ራዕይ ይዞ መንቀሳቀስን ግንዛቤ በመያዝ ወደ ሐዲዱ መግባት ተጀምሮዋል፡፡ ለዚህም በአደረጃጀት በአሰራርና በሰው ሀይል የተጠናከሩ ተግባራትን መፈፀም ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የሰው ሀይላችን በእውቀትና በክህሎት የበቃ መሆን ያለበት ብቻ ሳይሆን ልማታችን የሞት ሽረት ጉዳይ እንደሆነ አመለካከቱን የያዘ የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት የሚንቀሳቀስና የዲሞክራሲ እሴቶችን የስነ ምግባር መርሆዎችን ውስጣዊ አድርጎ የችግሮች ሁሉ መፍቻ በዚህ እና በዚህ ብቻ መሆን እንዳለበት እምነት ይዞ በተግባር የሚያዋህድ እንዲሆን የማብቃትና ሲቪል ሰርቫንቱ ራሱ በዚህ ውስጥ ሆኖ ሌሎችንም ወደዚህ ለማምጣት የስበት ሀይል ያለው እንዲሆን ተቃኝቶ ነው እየተሰራ ያለው፡፡.... ተጨማሪ>>