መስከረም 14 2002ዓም>>>
ለ28 አመራረሮችና ባለሙያዎች መሠረታዊ ኮምፒዉተር ሥልጠና ተሰጠ::
በሸካ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ የተቋቋመው ጊዜያዊ የኮምፒዩተር ሥልጠና ማዕከል የዞን አመራሮችና ባለሙያዎችን መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትን ለማስጨበጥ የስልጠና ማኑዋል ተዘጋጅቶ አንደኛው ዙር ከነሐሴ 1/2001 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 40 ቀናት ወይም ለ 160 ሰዓት 28 አመራሮችና ባለሙያዎች ሥልጠናዉ ተሰጥቶ ካበቃ በኋላ በመስከረም 14/2002 ዓ.ም ሠልጣኞች መመረቃቸዉን የዞኑ አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ ተሸመ ኃይሌ አስታዉቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የ2ኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኃላፊዉ አክለዉ ገልፀዋል፡፡