ታህሣሥ 10 2001ዓም>>>
ከታህሣሥ 10/2001 ዓ.ም ጀምሮ ደልዳይ ኮሚቴዎች ተዋቅረዉ እስከ ጥር 30 2001 ዓ.ም በዞን፣በወረዳና በአስተዳደር አቅም ግንባታ ሰሥር የሚገኙ 7 ሰክተር መ/ቤቶች መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሸካ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሸመ ኃይሌ መሎ አስታወቁ፡፡ በዚሁ መሠረት በየደረጃው ባሉ ሰባት ሰክተር መ/ቤቶች ከዞን እስከ ወረዳ ያለው የሥራ ሂደት መዋቅር 1373 የሰው ሀይል የሚያስፈልግ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በየመዋቅሩ መስፈርቱን አሟልቶ የተመደበው የሰው ሀይል 648 (47.19%) መሆኑ ተረጋግጋጧል፡፡ በትምህርት ዝግጅት ማነስ ምክንያት 107 ሰራተኞች በድልድሉ ሊታቀፉ አልቻሉም ሲሉ የሸካ ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ የሰዉ ሀብት ልማት አስተባባሪ ገለፁ፡፡