መጋቢት 5 2001ዓም>>>
የዞኑ አቅም ግንባታ መምሪያ ቁልፍ ተግባር የነበረው ምርጥ ተሞክሮ መቀመር ከመምሪያው የተዉጣጡ አራት ባለሙያዎችን ወደ ወረዳ በማሰማራት የተሰራ ሲሆን በዚህም በመሰረት በተመረጡ አለታወንዶ ፣ ዳሌና ሸበዲኖ ወረዳዎች ላይ የመስክ ግምገማ ተደርጎ የምርጥ ተሞክሮ ሰነድ ተቀምሮ መጋቢት 3, 2001ዓ.ም ለክልሉ አቅም ግንባታ ቢሮ ተላልፏል፡፡ በዚሁ መነሻ በክልሉ አቅም ግንባታ ቢሮ አስተባባሪነት ከ13 ዞኖችና ከ8 ልዩ ወረዳዎች የተዉጣጡ የአቅም ግንባታ መምሪያ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ምርጥ ተሞክሮ በተገኘበት በዳሌ ወረዳ የአጃዋ ቀበሌ በአቶ ዉዴ ጉዬ ማሳ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡