ነሀሴ 16 2000ዓም>>>
የዞኑ አቅም ግንባታ መምሪያ በ2000 ዓ.ም የመጀመሪያ ተግባር ያደረገው በ2000ዓ.ም የተሻለ የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ላሳዩ ከ19ኝ የገጠር ወረዳዎችና ከ2 የከተማ አስተዳደሮች ግንባር ቀደም ለሆኑ አቅም ግንባታ ጽ/ቤቶች መሸለምና ለሌሎች ደረጃቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት መስጠት ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ነሀሴ 16, 2000 ዓ.ም በሲዳማ ዞን አስተዳደር አዳራሽ በአፈፃፀማቸው እኩል ነጥብ በማምጣት በ1ኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ለዳሌና ለአለታወንዶ አቅም ግንባታ ጽ/ቤቶች እያንዳንዳቸው 1 ዲጂታል የቪድዮ ካሜራ የተሸለሙ ሲሆን በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የአርቤጎና ወረዳ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኮምፒዩተር ተሸልሟል፡፡ በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ በመገኘት የሸለሙት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሰው ገብሬ እና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሴ ዳልኬ ናቸው፡፡ በዚህ ደረጃ አወጣጥ የመጨረሻ ደረጃ የያዙት ይርጋአለም ከተማ፣ ሎካ አባያ እና ወንዶ ገነት ናቸው፡፡