e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

Our Links
SNNPRS Capacity Building
All Zonal Civil Service Departments
All Woreda Capacity Building Offices
Action Aid
Aynage Project
Silite Development Associations
Our Customers
Last Updated Friday, December 4, 2009 8:24 PM
 
note
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የአገራችን በየዘርፉ የተቀረጹትን ፖሊሲዎች ወደ ተግባር ለማሸጋገርና እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂነት ለማረጋገጥ በአሰራር፣በአደረጃጀትና በአመለካካት የተለወጠ፣ የልማት እንቅስቃሴውን በብቃት ሊመራ የሚችል መንግስታዊ ተቋም ሊኖር እንደሚገባ ይታመናል፡፡
የመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎት (መንግስታዊ አገልግሎት) ኅብረተሰባችን ከደረሰበት ማህበራዊ ንቃት እና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ብቁ ሆኖ ለመገኘት የሚያስችላቸውን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችል ለማድረግ ከወቅቱ ጋር የተጣጣመ የአደረጃጀትና በአገልግሎት ገበያው ውስጥ ተፈላጊ ሆኖ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከዚህም አንጻር ያለውን ክፍተት በማስወገድ ረገድና የልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውን ለማፋጠን በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎች የተከናወኑና በርካታ ለውጦችም ተመዝግቧል፡፡ በከፊል ሴክተሮች መተግበር የጀመረው የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ትግበራ በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥና የአፈጻጸም ለውጥ እንዳለ በተጨባጭ የታየ ጉዳይ ነው፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም በቀሪዎቹ ሴክተሮች የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጡን በመተግበር በሁሉም የመንግስት ተቋማት እንደ ሥርዓት እንዲተከል ለማድረግ የተጠናከረ የድጋፍና የክትትል ሥርዓት መዘርጋትና የተጠናከረ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ተግባር ነው

 
 
 
 
Copyright © Silte Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official Silte Zone Capacity Building Website