መስከረም 4 2002ዓም>>>
የዞኑ አቅም ግንባታ መምሪያ አመታዊ ጉባኤ ከመስከረም 4-5 በስልጤ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በጉባኤ የአቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ የመምሪያውን የ2001 ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ የሁሉም ወረዳ ኃላፊ ተራ በተራ የ2001 ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡በቀጠይነትም በቀረቡ ሪፖርቶች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎ በመልካም አስተዳደር፤ በፍትህ ስርዓት ማሻሻያና በሌሎችም በተስተዋሉ ክፍተቶች ዙሪያ እያንዳንዱ ወረዳ በንቃት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አቋም ተይዟል፡፡ ለጉባኤው በተያዘው መርሃ-ግብር መሰረት በአቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ በአቶ ሬድዋን ኑሪና በዘጠኙም አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች መካከል የግብ ስምምነት መፈራረም ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡ በጉባኤው የስምንቱም ወረዳና ወራቤ ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የየስራ ሂደት አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በመጨረሻም በ2001 በጀት ዓመት በአንጻራዊነት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት ጉባኤው ተጠናቋል፡፡