ነሐሴ 19 2001ዓም>>>
ከሰኔ 1 ጀምሮ እስከ ነሃሴ 12 2001 ድረስ ሲሰጥ የቆየው የመሰረታዊ የኮምፕዩተር ሥልጠና ምረቃ ስነ-ስርዓት ነሃሴ 19 2001 ዓ.ም በስልጤ ዞን አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡በስነ-ስርዓቱ ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች፣ተመራቂዎችና የአቅም ግንባታ መምሪያ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን በፕሮግራሙ የአቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሬድዋን ኑሪ የፕሮግሙን መክፈቻ ንግግር አድርገው በመቀጠልም የኢኮቴ መሰረተ ልማት አቅርቦትና አገልግሎት የስራ ሂደት በስልጠናውና በስራ ሂደቱ ተግባራት ዙሪያ በስራ ሂደቱ አስተባባሪ በአቶ መሀመድ ኑርሰቦ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በስልጠናው ሂደት፣በታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ዙሪያ ከተመራቂዎች በተነሱ አስተያየቶች መነሻ ውይይት ተደርጓል፡፡በመጨረሻም ለተመራቂዎች ሰርተፊኬት በትምህርታቸው ብልጫ ላመጡ ሶሳት ተመራቂዎች እንደየደረጃቸው የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቶ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡