|
የዞናችን ብሎም የአገራችን ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ድህነት መሆኑን በግልፅ ተረድተን በልማትና መልካም አስትዳደር እምርታ ለማምጣት ስትራቴጅ ቀይሰን ድህነትን ፊት ለፊት መፋለም ከጀመርን ወዲህ ባለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት ተጨባጭ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችለናል፡፡
የተመዘገበዉ የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት እንድኖረዉ ከአሠራር የሥራ ሂደት ጋር ተያይዞ ያለዉን ዉስብስብ ችግር ከሥር መሠረቱ መንግሎ ለመጣል የገጠር ወረዳ መልካም አስተዳደር ፓኬጅ በመቅረፅ የስቭል ሰርቭስ ማሻሻያ እና የፍት ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም ተግባራዊ ከመደረጉም ባሻገር በቅርቡ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ/BPR/ በዞናችን በሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ /BPR/ በሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች ተግባራዊ በመደረጉ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል፡፡በመልካም አስተዳደር ረገድም ለዘመናት የነበሩ ችግሮች በመፈታታቸዉ የዜጎች ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተከብሯል፡፡
በድህነት ላይ የከፈትነዉ ዘመቻ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች የመልካም አስተዳደር መርሆን መሠረት በማድረግ መልካም ተመክሮዎችን ወደ ሁሉም አካባቢዎች በማስፋፋት መፈፀም እንዳለባቸዉ የዞኑ አቅም ግንባታ ዛረም እንደ ትላንቱ የሴክተር መ/ቤቶች የማስፈፀም አቅም እንድጠናከርና የተጀመረዉ ለዉጥ ተጠናክሮ እንድቀጥል በፅናት ይሠራል፡፡ በመልካም አስትዳደር እምርታ በማምጣት የኢትዮጵያን ህዳሴ እዉን እናደርጋለን፡፡
አቶ መልካሙ ዘሮ ደቅላቦ
የደ/ኦሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና
የአቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ
|