e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Friday, December 4, 2009 9:37 PM
 
note

መስከረም 19 2002ዓም>>

 new በደቡብ ኦም ዞን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ትግበራ ከተጀመረ ወዲህ ለውጦቶች እየተመዘገቡ ነው፡፡

headline በክልላችን በ2 ዙር የተጠናው የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት በመጀመሪያ ዙር በደቡብ ኦሞ ዞንም በ7 ሴክተሮች ወደ ሙሉ ትግበራ ከተገባ እነሆ 9ኛ ወር ላይ ደርሰናል ፡፡ እስካሁን ባለው አፈፃፀም በ7ቱ ሴክተሮች በድጋፋዊ ክትትል ወቅትና በግብረ ሀይል ከተደረገው ግምገማ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቀሙት የሚያሠራ ያህል የሰው ሀይል የተመደበባቸው የሥራ ሂደቶችና ምቹ የቢሮ አደረጃጀት ባለባቸው ተቋማት ተገልጋዩች ላይ ውጣ ውረድ ሳይበዛ አገልግሎት ከአንድ ቦታ ብቻ ማግኘት መቻላቸው ፈፃሚዎችም የሚሰጡትን አገልግሎት በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መንፈስ የሥራ ኃላፊዎችን ሳይጠብቁ ከጫፍ እስከ ጫፍ መፈፀምና መወሰን በመጀመራቸው የተገልጋይ መጉላላት መቀነሱ ፈፃሚዎች ከግል ውጤት ይልቅ ለተቋም ውጤት ትኩረት በመስጠት የቲም መንፈስ መፈጠሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ካደረግነው የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንደሚባለው የአባቶታችን አባባል ጅምሩ ተስፋ ሰጪ መሆኑን በዞኑ አቅም ግንባታ መምሪያ የለውጥ ኘሮግራሞች ኘሮጀክት ጥናትና ትግበራ ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዓለሙ ወ/ ሥላሴ ገልፀዋል ፡፡

  • በመቀጠልም ከ7ቱ ሴክተሮች የተገኙ ልምዶችን በመቀመር በ2ኛ ዙር ወደ ሙሉ ትግበራ ለተሻገሩት ሌሎች ሴክተሮች ቀጣይነት ያለው በቼክ ሊስት የታገዘ ድጋፋዊክትትልለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን አመልክተዋል ፡፡
  • በመያያዝም የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ / BPR / ትግበራን በሁሉም የመንግሥት ተቋማት እንደ ሥርዓት ለመትከል የተጀመረውን ጉዞ ከማጠናከር ባሻገር በተያዘው የ2ዐዐ2 በጀት ዓመት በመልካም አስተዳደር ፖኬጅና በፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ኘሮግራም ላይ ትኩረት እንደሚደረግ በተለይም በገጠር እና በከተማ ከህብረተሰቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ተቋማትና ለቅሬታ መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዩችን በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተጠናከረ መልኩ ለመፈፀም ጥረት እንደሚያደርጉ አክለው ገልጸዋል፡፡
 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 . . . Next>>
 
Copyright © South Omo Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official South Omo Zone Capacity Building Website