e f a  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Friday, December 4, 2009 9:37 PM
 
note

መስከረም 10 2002ዓም>>>

 new በደቡብ ኦሞ ዞን BPR እና የሰው ሀብት ስምሪት ጥናት ተካሄደ፡፡

headline መሠረታዊ የሥራ ሂደት ከክልል ጀምሮ በሰባት ሴክተር መሥሪያቤቶች ላይ ተጠንቶ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ወደ ሙሉ ትግበራ የገቡ ግብርናና ገጠር ልማት፣ ትምህርት፣ ሥራና ከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዲስትር፣ አቅም ግንባታ ፣ፋይናንስ ኢካኖሚ ልማትና ፍትህና ፀጥታ መምሪያ (ፖሊስና ማረሚያ )ሲሆኑ በነዚህ መስሪያቤቶች ላይ ተጠንቶ የተተገበረዉ 31 ዋና እና 3 ደጋፊ ባጠቃላይ 34 የሥራ ሂደቶች መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡
በ34 የሥራ ሂደቶች ወደሙሉ ትግበራ የገቡ በዞን መምሪያዎችና በወረዳ ተመሳሳይ የሥራ ሂደቶችም ቢሆን በየደረጃዉ የተመደበና ክፍት የሆነ የሥራ ሂደት መለየት በማስፈለጉ ተደጋግመዉ ሲቆጠሩ 375 የሥራ ሂደቶች ዉስጥ የሰዉ ኃይል ያልተመደበበት 158(42.32%)፤ 1 - 74.99% ድረስ የሰዉ ኃይል የተመደበበት 116(30.93%)፤75% እና በላይ የሰዉ ኃይል የተመደበበት 101(26.93%) ይሆናል፡፡

የሥራ ሂደቱ ተጠንቶ ወደሙሉ ትግበራ ከገቡ ሰክተሮች የሚጠበቀዉን ዉጤት በዝቅተኛ ወጪና ጊዜ፣ጥራት ያለዉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ወይም ምርት ለማግኘት የሚቻለዉ 75% እና በላይ የሰዉ ኃይል የተመደበ እንደሆነ ጥናቱ ያመለክታል፡፡
በ375 በዞን፣ በወረዳና በጂንካ ከተማ አስተዳደር ባሉት የሥራ ሂደቶች ላይ የሚያስፈልግ የሰዉ ኃይል 1363 የተመደበ 438(32.13%) ክፍት መደብ 925(67.7%) ሲሆን ከክፍት መደቦች የመጀመሪያ ዲግሪና በላይ የሚጠይቁ 187(20.22%) ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ የትምህርት ደረጃ የሚይጠቁ መደቦች 738 (79.78%) ይሆናሉ እስከ75% ለሟሟላት 582የሰዉ ሀይልና ለአንድ ወር ደመዎዝ የበጀት መጠን ብር 695114.00 ሚያስፈልግ ይሆናል ( ገጽ 6 እና 7፣8፣ ይመልከቱ)

ትክክለኛ የሰዉ ሀብት በትክክለኛ ቦታ ከመደብ አንጻር በተጠኑ መሥሪያ ቤቶች 75% የሰዉ ሀይል ለመማሟላት ከሚያስፈልገን 582 የሰዉ ሀይል ዉስጥ 188(32.30%) በተፈጥሮ(የእፀዋት እና የእንሰሳት) ሣይንስ ፣ 323(55.5%) በኢኮኖሚክስ፤ በማናጅመንት፤ በአካዉትግ፣ተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ በማስተማር ፣ትምህርት አስተዳደር፣የትምህርት እቅድ ዝግጅት፣ ጂኦግራፊ፣ፖለቲካል ሳይንስ፣ማነጅመንት፣በህግ፣ ሶስዮለጂ እና ተዛማጅ፣71 (19.20%) የስቪል፣የህንፃ፣የከተማ ምህንድስ፤ቅየሳ ፤የከተማ ፕላንና ወዘተ ሙያዎች ፣ በመሆኑን በመጀሪያ ዙር መሰረታዊ የስራ ሂደት ትግበራ የሰዉ ሀይል ድልድል እንደሆነና 2ኛ ዙር በሚቀትለዉ ጥናት ተካቶ እንደሚቀርብ የስራ ሂደቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዓለሙ ወልዴ ገልጸዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 . . . Next>>
 
Copyright © South Omo Zone CBB 2009 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official South Omo Zone Capacity Building Website