በክልላችን እንዲሁም የክልላችን አካል በሆነው ዞናችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥና ከልማቱም ሕዝቡ በበየደጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ሥራን ማጎልበት ወሳኝ ነው ፡፡ ይህን ለማሳካት ቀደም ሲል በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራም ፣በፍትህ ማሻሻያ ኘሮግራም እንዲሁም ባልተማከለ የወዳ አቅም ግንባታ ኘሮግራም በመታዝ በተከናወኑ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በዞናችን ያሉ የመንግሥት ተቋማት የማስፈፀም አቅም እየጎለበተ መጥቷል ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በመንግሥት ተቋማት ያለው አደጃጀት ፣ አሠራርና የሰው ኃይል ሁኔታ ሲታይ በልካም አስትዳደር ማስፈን እና ዴሞክራሲ ግንባታ ሥራችን መጎልበት የሚፈልገውን አስተዋጽኦ በሚያበረክት ደረጃ አይደለም፡፡ ስለሆነም በመንግሥት ተቋማት ቀልጣፋና ግልጽ አሠራር በማስፈን በአገልግሎት አሰጣጥ የኀብረተሰቡን ፍላጐት በማርካት ሕብረተሰቡን ለልማት በማነሣሣት በክልላችን እንዲሁም በዞናችን ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ የመሠረታዊ አሠራር ሂደት ለውጥ በክልል ደረጃ ተጠንቶ በመጀመሪያ ዙር በ7 ሴክተሮች ተግባራዊ ከመሆኑም በላይ በ2ኛው ዙር ጥናቱን ያጠናቀቁ ሴክተሮችም የሙከራ ትግበራቸውን አጠናቀው አሁን ወደ ሙሉ ትግበራ እየገቡ ናቸው ፡፡...ተጨማሪ>>
መስከረም 21 2002ዓም>>>
በሁለተኛ ዙር ለሙሉ ትግበራው ጥናታቸውን ያጠናቀቁ 9 ሴክተሮች የሠራተኞች ድልድል በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ ጀምሮ እንዲገቡ ያላለሰለሰ ጥረትና ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በአሁን ወቅት በሁሉም መንግሥት ተቋማት መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ እየተተገበረ ሲሆን ትግበራዉ በታቀደው መሠረት በመጀመሪያ ዙር በ7 ሴክተሮች በተሳካ ሁኔታ ሙሉ ትግበራ እንዲከናወንና በሁለተኛ ዙር ለሙሉ ትግበራው ጥናታቸውን ያጠናቀቁ 9 ሴክተሮች የሠራተኞች ድልድል በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ ከ21/1/2ዐዐ2 ጀምሮ እንዲገቡ ያላለሰለሰ ጥረትና ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ..... ተጨማሪ>>
ለ22 የቀበሌ ስራ አስኪያጆች ስልጠና ተሰጠ፡፡