f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Monday, June 20, 2011 12:28 PM
   
note  


headlineየክልሉ መንግስት በክልሉ መልካም አስተዳደርን በማስፈን የዳበረ ዴሞክራሲዊ ስርዓትን በመገንባትና በልማቱ መስክም ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው  እድገት በማስመዝገብ ክልሉን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማውጣት  ያላሰለሰ ጥረት  በማድረጉ ሰፊውን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ለውጦች በመመዝገብ ላይ ይገኛሉ ፡፡የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮም የለውጡ አጋዥ በመሆን የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት በክልሉ ቁልፍ ችግር የሆነውን የማስፈፀም አቅም በመገንባት በሰው ኃይል ፣ በአሰራርና ፣በአደረጃጀት ጠንካራ አቅም በመፍጠር የልማት እንቅስቃሴውን በብቃት ሊመራ የሚችል መንግስታዊ ተቋማት ፣አመራሮችና የሰው ኃይል መፍጠር ዋንኛ ተግባሩ አድርጎ  በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡መንግስታዊ አገልግሎትን የሚፈልገው ህዝብ ፍላጎት እያደገ መምጣት ፣በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገና እየጠነከረ የመጣው ውድድር  ከነዚህ መሰረታዊ ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣም መንግስታዊ ተቋማት አሰራር ቀልጣፋ መሆን የግድ በሚልበት ሁኔታ ላይ የምንገኝ  በመሆኑ በክልላችን  በመልካም አስተዳደር እመርታ ለማምጣትና የልማት ሂደቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉበት ሁኔታ መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተግባራዊ ተደርጎ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ፡፤ይህንን የለውጥ ሂደት ዘላቂና የተሳካ ለማድረግ የክልላችንን የልማት ኃይሎች የማስፈጸም አቅም በተከታታይ በመገንባት ሲቪል ሰርቪሱ ብቃት ያለው፣በስነ ምግባር የታነፀና ውጤታማ እንዲሆን የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን ቀጣይነትና  ዘላቂነት ባለው ሁኔታ በመተግበር ቅንጅታዊ አቅም በመፍጠር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ፡፡ በቀጣይም በክልሉ ያሉ የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ እና የውጤት ተኮር ስርዓት   ተግባራዊ መደረጉን በማረጋገጥ' የሲቪል ሰርቪስ የሰው ኃይል በቀጣይነት የሚለማበትንና ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት በመቀየስ እንዲሁም የመንግስት ዘርፍ አቅም ግንባታን በማጠናከር አገልግሎቱ የሚሻሻልበትና ውጤታማ የሚሆንበትን ስራ በመስራት በክልላችን ተጨባጭ ለውጥ በማስመዝገብ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ  በአመለካከቱ  የተስተካከለ ' የስራ ትጋትና ተነሳሽነት ያለው 'የአሰራርና የአደረጃጀት ችግሩ የተፈታለት ' ለውጤት የሚተጋ ሲቪል ሰርቪስ በክልላችን ለመገንባት ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን ፡፤

አመሰግናለሁ!!

 
Copyright © SNNPRS CBB 2010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPRS Capacity Building Bureau Website