
|
 |
ተልዕኮ |
 |
| የማስፈጸም አቅም ክፍተትን በመለየት ክፍተት መሙላት የጥናት መነሻ ሀሳቦችን በማቅረብ የሪፎርም ጥናቶች በማስጠናት አዳዲስ አሰራርና አደረጃጀት ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ስልጠና' የስልጠና ምክር አገልግሎት በአስቀጣይ ተቋማት ወይም በግል / በተቋም አማካሪ አካላት በማሰጠት የአፈጻጸም ክትትል ድጋፍና ግምገማ በማድረግ የለውጥ ፕሮግራሞችን መምራት ማስተባበርና ማስተግበር ነው ፡፤ |
ዓላማ |
| |
| ጎታች ነባርና ውጤት አልባ የሆኑ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በአዳዲስ አሰራሮች በመተካትና በማስተግበር የተለወጡ ወይም የማስፈጸም አቅማቸው የተገነባ ተቋማትን መፍጠር ነው ፡፡ |
| |
ዝርዝር ዓላማ |
| |
የማስፈጸም አቅም ችግሮችን ወይም ክፍተቶችን በየጊዜው በጥናት በመለየት የአፈጸጸም
ክፍተት እንዲሞላ ማድረግ ፡-
- ቀልጣፋ ውጤታማና ተገልጋይ ተኮር የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት ፡-
-የመንግስትን ገንዘብ እና ንብረት አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓት ቀልጣፋ ውጤታማና
ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ ፡-
- መልካም ስነምግባር ያለውና ብልሹ አሰራርን የማይቀበል ሲቪል ሰርቪስ መፍጠር ፡-
- በጥናት የተገኙትን አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን ለመተግበር የሚያስችል ስልጠና
በማሰጠትና የማስፈጸም አቅምን በዘላቂነት በመገንባት መልካም አስተዳደር ማስፈን ፡-
- ከስልጠና በተጨማሪ ትግበራውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ስርዓት በመዘርጋት አቅም መገንባት፡-
|
| |
የሚሰጠው አገልግሎት |
| |
- የአፈጻጸም ከፍተትን መለየት፤
- ጥናት እንዲካሄድና የማስፈጸም ሰነድ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
- በፓይለት የተፈተሸ የማስፈጸሚያ ሰነድ መረከብ፤
- የትግበራ ዕቅድ ማዘጋጀትና ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤
- የትግበራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- የፋይዳ ግምገማ ማድረግ፤
- የጥናት ሥራውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራሞችንና የሪፎርም ተግባራትን ይመራል ፤ ይደግፋል ፤ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤
|

|
የስራ ሂደቱ ዓላማ |
 |
- የሲቪል ሰርቪስ የቅሬታ እና ይግባኝ አገልግሎት ተደራሽ 'ቀልጣፋ 'ወጪ ቆጣቢ ጥራት ያለውና ፍትሀዊ እንዲሆን ማድረግ ፡-
- ምቹና ወቅታዊ የቅሬታና ይግባኝ አወሳሰን ስርዓት መዘርጋት
- የተገልጋዮችን የእርካታ ደረጃ በመገንዘብ ተገቢነት ያላቸውን መፍትሄዎች ማመንጨት ፡-
- በተገልጋዮች መካከል መልካም የስራ ግንኙነት መፍጠር ፡-
|
ተልዕኮ |
| |
- ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበትን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ' በተገልጋይ ፍላጎት ላይ በመመስረትና ውጤት ተኮር አገልግሎት አሰጣጥን በማረጋገጥ የስራ ሂደቱን የግብ ስኬት እውን ማድረግ ነው ፡፤
|
| |
ራዕይ |
| |
- በስራ ሂደቱ የረካ ተገልጋይና ለልማትና መልካም አስተዳደር መስፈን አጋዥ የሆነ የስራ ግንኙነት ተፈጥሮ ማየት ፡
|
| |
የስራ ሂደቱ አገልግሎቶ |
| |
- ለቅሬታ ውሳኔ መስጠት ፡-
- ለይግባኝ ውሳኔ ወይም መፍትሄ መስጠት ፡-
- ለይግባኝ ማስፈቀጃ ጥያቄ ውሳኔ መስጠት ፡-
- ለትዕዛዝ ይነሳልኝ ጥያቄ ውሳኔ መስጠት ፡-
- ለመሰየም ጥያቄ ውሳኔ መስጠት ፡-
- የምክር ድጋፍና ክትትል አገልግሎት መስጠት ፡
|
| |

|
| |
ሂደቱ ከተቋሙ የወሰደው ተልዕኮ |
| |
- ዘመናዊ ቀልጣፋና ለለውጥ ዝግጁ የሆነ የሰው ሀብት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት በሴክተሩ ለሚካሄደው ልማትና ለመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ፡-
|
| |
| የስራ ሂደቱ ዓላማ |
| |
- ለመልካም አስተዳደርና ልማት አጋዥ የሆነ ተገልጋዩን የሚያረካ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የሰው ሀብት አመራር መፍጠር ፡-
|
| |
በዋናው የስራ ሂደት የሚሰጡ አገልግሎቶች |
| |
- መመሪያዎችን 'የአፈጻጸም መስፈርቶችን ማዘጋጀትና ማስተዋወቅ ፡-
- ተጠንተው የሚመጡ አዳስ የሰው ሀብት ስራ አመራር አሰራሮችን ማስተዋወቅ' ማሰልጠን
- የስራ ደረጃ ምዘናና ጥቅማ ጥቅም በማጥናት ማስወሰን /መወሰን/
- የሰው ሀብት ስራ አመራር የአሰራር ድጋፍና ክትትል ሰነዶችን ያዘጋጃል ፡-
- የድጋፍና ክትትል አገልግሎት ይሰጣል 'ማስተካከያዎችን ያደርጋል' ግብረመልስ ይቀበላል ፡-
- የሰው ሀብት ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ መፍትሄዎችን ማፍለቅና ተግባራዊነታቸውን መከታተል ፡-
- ለተገልጋዮች የምክርና ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል ፡
|

|
የስራ ሂደቱ ዓላማ |
 |
| |
- የሰው ሀብት መረጃና ተዛማጅ ሪከርድ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአግባቡእንዲደራጁ በማድረግና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት በመፍጠር የክልሉ የተጠቃለለ የሰው
ሀብት ስታትስቲካል መረጃ በተሟላና በተፈለገው አይነት ለማጠናቀር ያስችላል ፡፤በከልሉ በየደረጃው በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና በአንድ ማዕከል የፔርሶኔልና ተዛማጅ መረጃዎችን ወጥ በሆነ ሥርዓት በማደራጀት ቀልጣፋ የሪከርድ አገልግሎት መስጠትና ከተደራጀው የፔርሶኔል መረጃ የተዘጋጀው የሰው ሀብት ስታትስቲካል መረጃ አሰባስቦ በአንድ ላይ በማጠናቀር መተንተንና ለተገልጋዮች ማሰራጨት ነው ፡፤ |
| |
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት |
| |
- የሰው ሀብት ፔርሶኔልና ተዛማጅ መረጃዎችን ማደራጀት፡-
- የሪከርድና ማህደር አገልግሎት መስጠት ፡-
- የፔርሶኔል ሪከርድ በኮምፒውተር ማደራጀት ፡-
- የሰው ሀብት ስታትስቲካል መረጃ ማሰባሰብ 'ማጠናቀር ' መተንተንና ማሰራጨት
- የስራ ሂደቱን ዕቅድና ሪፖርት ማዘጋጀት -
- በሪከርድ አያያዝ በስታትስቲካል መረጃ አጠነቃቀር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠትና ድጋፋዊ ክትትል ማድረግ ፡
|

|
የስራ ሂደቱ ዋና ዋና አገልግሎቶች :- |
 |
| |
- የስራ ደረጃ ምዘና እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን በየደረጃው ከሚገኙ የሴክተሩ ሂደቶች ሲቀርብ በመስፈርቱ መሆኑን በማጣራት ለዋናው ሂደት ማቅረብ ፡-
- የሰው ሀብት ዕቅድ ማዘጋጀት ፡-
- የሰው ሀብት ማሟላት ፡-
- በየደረጃው የተከናወኑ የማሟላት ስራዎችን መመዝገብና ስህተቶች ካሉ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰዱ ማድረግ ፡-
- የሰው ሀብት መምራት / ማትጋት መደገፍ 'የዲሲፒሊን እርምጃ መውሰድ /
- ዞኖች 'ማዕከላትና ልዩ ወረዳዎች ድጋፍ'ክትትልና የምክር አገልግሎት ሲጠይቁ መስጠት ፡-
- ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ጥቅማ ጥቅሞች መሟላታቸውን ምቹ የስራ ሁኔታ መፈጠሩን መከታተልና ማረጋገጥ ፡-
- የዲሲፒሊን ጉዳዮችን መርምሮ የውሳኔ አስተያየት ማስተላለፍ ፡-
- ቅሬታ ተቀብሎ ማስተናገድ
- የአገልግሎት ማቋረጥ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ፡-
|
| |
|
| |
ይህ የስራ ሂደት ተጠሪነቱ ለተቋሙ መሪ ወይም የተቋሙ መሪ ለሚወክለው ኃላፊ ሆኖየሚከተሉት ስልጣንና ኃላፊነቶች ይኖሩታል ፡- |
 |
| |
1 የረጅምና የመካከለኛ ዘመን የሲቪል ሰርቪስ ሴክተርን ኘሮግራሞች ዕቅድ ማዘጋጀትና መከለስ
2 የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ዓመታዊ ዕቅድ፣ የድርጊት መርሃ ግብር፣ በጀት ፣ የአፈፃፀም ተሳትፎ
ስምምነት ማዘጋጀትና መፈራረም ፡-
3 የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ስራን መገምገም 'የቴክኒክ ድጋፍ መስጠትና ማፅደቅ ፡-
4 የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ እቅድ አፈጻጸም መከታተል ድጋፍ መስጠት፣ መገምገምና ሪፖርትና ግብረመልስ
ማዘጋጀት
5-- የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ፕሮግራሞችን / ፕሮጀክቶችን / የእርዳታና ብድር በጀት ማስተባርና መከታተል ፡-
6 በግማሽ ዘመን የአፈጻጸም ግምገማ ውጤት መሰረት የቀጣዩን ግማሽ ዓመት የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች
እቅድ እንደአስፈላጊነቱ ሪቪው በማድረግ የተከለሰ የልማት ዕቅድ ያዘጋጃል ፡ |
| |
በስራ ሂደቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችና ተግባራት |
| |
- የሚመለከታቸውን በማሳተፍ በተሟላ ሁኔታ የተዘጋጀ የልማት ዕቅድና
- ፕሮጀክቶች አዘገጃጀት 'አፀዳደቅና አፈጻጸም ስርዓት ፡-
- የሚመለከታቸውን በማሳተፍ በተሟላ ሁኔታ የተዘጋጀና የፀደቀ የልማት ዕቅድ አዘገጃጀት መመሪያና ማኑዋል ፡-
- የሚመለከታቻን በማሳተፍ በተሟላ ሁኔታ የተዘጋጀና የጸደቀ ጠቋሚ የ 10 ዓመትና የ5 ዓመት የልማት ዕቅድ 'ተንከባላይ የመካከለኛ ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ዓመታዊ ዕቅድና በጀት ሰነድ ፡-
- በየበጀት ዓመቱ የተገመገሙ (ቅድመ ትግበራ ግምገማ ) የልማት ፕሮጀክቶችና የተዘጋጁ የግምገማ ሰነዶች ፡-
- የሚመለከታቸውን በማሳተፍ ( ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ) በየበጀት ዓመቱ የተዘጋጁና የፀደቁ የየሩባ ዓመቱ የተጠቃለለ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ፡-
- የሚመለከታቸውን በማሳተፍ የተዘጋጁና የጸደቁ የልማት ዕቅድ የግማሥ ዘመን አፈጻጸም ግምገማ / Mid term Review / እና የመጨረሻ ዘመን አፈጻጸም ግምገማ / Terminal Evaluation / ሪፖርቶች ፡-
- በtmrጡ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ስኬቶችና ፋይዳዎች ላይ ግምገማዎችን በማካሄድ የተዘጋጁና በሚመለከታቸው አካላት በማስተቸት የጸደቁ ሰነዶች ፤
|
| |

|
ዓላማ |
 |
በሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ደጋፊ የስራ ሂደት ዋና አላማ በሴክተሩ ቀልጣፋ 'ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግስት ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን እንዲኖር በማድረግ ፖለቲካዊ ' ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እሴቶችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት ሲሆን የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት ፡-
- ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ፍሰት እንዲኖር ማድረግና በሀገሩ ጉዳይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ህብረተሰብ የመገንባቱን ሂደት ማጎልበት ፡-
- ቀልጣፋና ውጤታማ ኮሚዩኒኬሽን እንዲኖር ማድረግና መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያለውን ብቃት ማረጋገጥ ፡-
- በክልሉና በሀገሪቱ በመስፋፋት ላይ ያለውን ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የፈጠራቸውን እድሎችና በእነዚህ እንዴት በሰፊው መጠቀም እንደሚቻል ማስተዋወቅ :-
- በህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ዓብይ መርሆዎችና እሴቶች እንዲሁም በክልላዊና አገራዊ ጥቅሞች ላይ ብሄራዊ መግባባትን ማጠናከር ፡-
- በመካሄድ ላይ ባለው ለውጥ እየተፈጠረ ያለውን አዲስ እውነታ በስፋት በማስተዋወቅ የክልሉንና የአገሪቱን በጎ ገፅታ መገንባት ፡-
- ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ማስፋት
|
| |
የስራሂደቱየሚያከናውናቸውተግባራት
|
- የሥራ ሂደቱ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ 'ሥራ አመራር ተቋም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በተዋረድ በዞን፣ በወረዳና ልዩ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች በመንግስት ኮሚኒኬሽን ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራትን በመከታተል ያሳውቃል፣
- በሴክተሩ ስትራቴጂዎች፣ ኘሮግራሞች፣ ኘሮጀክቶች ዕቅድ አፈፃፀሞች እንዲሁም የህብረተሰቡን የልማት እንቅስቃሴና ውጤቶች በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብ እና በማጠናቀር እንደ ተገልጋይ ፍላጐት በህትመት፣ በገፅ ለገፅ፣ እና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን ያሰራጫል፡፡
- ሚዲያዎች ከሴክተሩ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ያስተባብራል፣ ዋና ዋና ሴክተራዊ በሆኑ ጉዳዮች፣ ክንውኖችና ሁነቶች የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ የሚዲያ ጥቆማ ይሠጣል :፡-
|
| |

|
ትርጉም
|
| የሥርዓተ ፆታ ጉዳዮችን የሁሉም የልማት ዕቅዶችና የስራ እንቅስቃሴዎች አንድ አካል አድርጎ በመውሰድ መተግበርና በዚህም ሴቶችና ወንዶች እኩል የልማት ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ማለት ነው፡፡ |
ራዕይ (Vision)
|
በሴክተሩ የሚታየው የስርዓተ ጾታ ክፍተት ጠቦ c?„‹ በአመራርና በውሳኔ ሰጭነት እንዲሁም በተለያዩ የሥራ መደቦች በሴክተሩና በሌሎችም ተቋማት ውስጥ ከወንዶች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ ሆነው ማየት፣ |
ተልዕኮ (Mission) |
በሥርዓተ ፆታ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ ጥናት በማካሄድ፣ የመፍትሄ ስልቶችን መቀየስና ማስፈፀም፣ በሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በየደረጃው የሚገኙ ተቋሟት ዕቅዶችን በመፈተሽና በአፈፃፀማቸው ላይም የቅርብ ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ በማድረግ፣ በሁሉም ፈፃሚ አካላት መካከል ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋት እኩል የስርዓተ ፆታ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡ |
ዓላማ / Objective / |
 |
|
| |
| ዓላማ |
 |
- በፀረ-ኤች -አይ-ቪ ኤድስ ዙሪያ የተጀመሩትን ስራዎች በመቀጠል ብቁና ልማታዊ ዜጋን ለማፍራት የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሰራተኞች የባህሪ ለውጥ
በማምጣት መከላከልና መቀነስ ፡-
|
| ግብ |
- የኤች አይ ቪ ኤድስ ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ሰራተኞችየባህሪ ለውጥ በማመምጣት ኤች አይ ቪ ኤድስን በመዋጋት እራሱን ቤተሰቡን
ጎረቤቱንና ህብረተሰቡን ከወረርሽኙ እንዲጠብቅ እንዲከላከል እንዲቀንስ
ማስቻል ፡
|
| የስራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት |
- የሴክተሩን የጸረ ኤች አይ ቪ /ኤድስ ዕቅድ ማዘጋጀት ፡-
- የተቋሙን ሰራተኞች ለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚጋልጡ ሁኔታዎችን ማሰስ ፡-
- የጸረ ኤች አይ ቪ / ኤድስ ትምህርት ' መረጃና የባህሪ ለውጥ ስርፀት ተግባራትን
- ማከናወን፡-
- በጸረ ኤች አይ ቪ /ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ ላይ የአጋርነት / ፓርትነርሺፕ ተግባራትን
- ማከናወን ፡-
- ተቋማዊና ነባራዊ የኤች አይ ቪ /ኤድስ ተጽእኖ የዳሰሳ ጥናት ማሄድ ፡-
- ተቋማዊ የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት ተግባራትን ማከናወን ፡-
- የጸረ ኤች አይ ቪ /ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ ተግባራትን አፈጻጸም መከታተልና መገምገም ፡-
- ዕቅድክንውንክትትልናግምገማማካሄድ፡
|

|
የስራ ሂደቱ ዓላማ |
 |
- የስራ ሂደቱ ዓላማ ከጊዜ'ከወጪና ከጥራት አንጻር የደንበኞችን / ተገልጋዮችን ፍላጎቶች ለማሟላትየሚችሉ የግዢ 'ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ተግባራን በማከናወን የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ
ስራዎችን በማካሄድ ችግሮችን በመለየትና ድጋፍ በመስጠት አስፈላጊ መረጃዎችንና የአፈጻጸምሪፖርት ተደራሽ በማድረግ የግብ ስኬቶችን ማሳካት ፡-
|
| የስራ ሂደቱ አገልግሎት |
| ክፍያዎች መፈጸም |
- ለመስሪያ ቤቶችና ለስራ ሂደቶች መደበኛና የካፒታለ በጀት ክፍያ መፈጸም ፡-
- የአደራና ተመላሽ ሂሳብ ክፍያ መፈጸም ፡-
- ከወጪ መጋራት የተሰበሰበውን ገንዘብ ማስተላለፍ ፡-
- የጡረታ አበል ክፍያ መፈጸም ፡-
- የረዥም ጊዜ የደመወዝ ብድር ክፍያ መፈጸም ፡-purchasing
- የልዩ ልዩ ፈንድ በጀት ገንዘብ ክፍያ መፈጸም ፡-
- የባንክ ሂሳብ ማስታረቅ ፡-
- የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ፡-
- ወርሀዊ የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ፡-
- ዓመታዊ የተጠቃለለ የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ፡-
- ለሚዛወሩ ሰራተኞች ክሊራንስ መስጠት ፡-
- በጀት ዝውውርና ሽግሽግ ፡-
|
| ግዢ የመፈጸም አገልግሎት |
- የግዢ ዕቅድ ዝግጅት ፡-
- የገበያ ዋጋ ጥናት ማከናወን ፡-
- የቀጥታ አገልግሎት ግዢ ፡-
- በጨረታ የሚፈጸም ግዢ ፡-
- የደመወዝ ክፍያ ፡-
- የውሎ አበል ክፍያ ፡
- የተሸከርካሪ አገልግሎት ጥገና ክፍያ ፡-
- የስልጠና ' የስብሰባ አበልና ትራንስፖርት ክፍያ ፡-
- የጥቃቅን አገልግሎት ክፍያ ፡-
|
| ንብረት አስተዳደር |
- የንብረት ገቢ ፡-
- የንብረት ወጪ ፡-
- ንብረት በትውስት መስጠት ፡-
- ወጪ የተደረገ ንብረት ተመላሽ ማድረግ ፡-
- ቋሚና አላቂ ንብረት መመዝገብ ፡-
- ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ንብረቶችን ማስወገድ ፡-
|
| የስራ ሂደቱ የማዕዘን ድንጋዮች |
- በጀት :-
- የሰለጠነ የሰው ኃይል :-
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ :-
- ብቃት ያለውና ቀና ስራ አመራር :-
- የባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮች ትብብር :-
- የስራ ሂደቱ ስልጣንና ;- ኃላፊነት
|
| |
 |
| |
 |
| የሥራ ክፍሉ ትርጉም፡ |
| |
- በመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ መልካም ሥነ-ምግባርን ለማስፈን ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና መቆጣጠር በሥነ ምግባር ኦፊሰር የሚመራ የሥራ ክፍል ነው፡፡
|
| |
| መግቢያ |
| |
- በመንግስት ተቋማት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸው፣ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን ማቋቋም በማስፈለጉ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 84/2003 የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች በክልል ተቋማት ተደራጅተው ከየካቲት 2003 ዓ-ም ጀምሮ ወደ ትግበራ ገብተዋል፡፡
- የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር የልማት፣ የመልካም አስተደዳርና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንቅፋቶች ስለሆኑ እነዚህን ችግሮች በቁርጠኝነት ታግሎ ምንጫቸውን በማድረቅ፣ ዜጎች ብቁና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት እንዲያገኙ በማድረግ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ማሳካት ከሁለም ዜጋ ይጠበቃል፡፡
|
| |
| ራዕይ |
| |
- በመልካም ስነ ምግባር የታነጸ ፣ከብልሹ አሰራርና ሙስና የጸዳ ሲቪል ሰርቪስ ተፈጥሮ ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ማየት፣
|
| |
| ዓላማ |
| |
- የስነ ምግባርንና የጸረ ሙስና ግንዛቤን በማስረጽ የነቃና ሙስናን የሚጸየፍ የስራ ሃላፊ ሲቪልሰርቫንት በሴክተሩ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፡
- የአሰራር ስርዓት ጥናት በማካሄድ የብልሹ አሰራሮችን ክፍተት መዝጋት
- የስነ ምግባር ደንብ ማዘጋጀትና ጥሰት ሲፈጸም የእርምት እርምጃ መውሰድ
|
| |
| የሥራ ክፍሉ ተግባርና ሃላፊነት |
| |
- በተቋቋመበት ተቋም መልካም ሥነ ምግባርን ለማስፈን በጸረ ሙስና ፖሊሲዎች ፣ህጎች፣ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ለተቋሙ ሃላፊዎችና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን ይሰራል፡፡
- የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራርን መከላከል ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎች የተቋሙን የበላይ ኃላፊዎች ያማክራል፤ የተቋቋመበት መስሪያ ቤት ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ይከታተላል፡፡
- በተቋሙለሙስናወንጀልናብልሹአሠራርተጋላጭየሆኑአሰራሮችንከኮሚሽኑጋርበማጥናትክፍተቶቹስለሚዘጉበትሁኔታየመፍትሄሃሳብያቀርባል፤ስለጥናቱውጤትተግባራዊነትክትትልያደርጋል
- በተቋሙ ውስጥ ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ወይም ሊፈጸም ይችላል ብሎ በተጠራጠረ ጊዜ ለኮሚሽኑ ወዲያው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
- በቅርበት የሚገኙ ሌሎች የስነ ምግባር አውታሮችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፣እንደአስፈላጊነቱ በጋራ ይሰራል፡፡
- ለተቋሙ የሥራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ አግባብነት ካላቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ያስጸድቃል ፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
- በተቋሙ የስነ ምግባር ጥሰቶችን የሚመለከቱ ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት በመ/ቤቱ ደንብና መመሪያ መሰረት በቀጣይነት መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ የውሳኔ ሃሳብ ለተቋሙ የበላይ ሃላፊ ያቀርባል፡፡
- በተራ ቁጥር 7 የተጠቀሰው ጥፋት ከባድ የስነ ምግባር ጥሰት ወይም የሙስና ወንጀል ነው ብሎ ካመነ ወድያውኑ ጉዳዩን ለኮሚሽኑ ያሳውቃል፡፡
- በተቋሙ ሰራተኞች ቅጥር፣ እድገት ዝውውር ፣ ስልጠናና የከፍተኛ ትምህርት እድል ፣ የእቃ ወይም የአገልግሎት ግዥን ወይም የማንኛውም ሌላ ውል በሚመለከት ደንብና መመሪያ ተጥሷል ብሎ ሲያምን ለተቋሙ የበላይ ሃላፊ ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ሪፖርት ያደርጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
- በተቋሙ የሚገኝ ሠራተኛ የሙስና አሰራርንና ብልሹ አሠራርን በማጋለጡ ማንኛውም ተጽእኖ እንዳይደርስበት ክትትል ያደርጋል፤ ተጽእኖ ያደረገ ወይም የቀጣ ካለ እያጣራ ከማስረጃ ጋር ድርጊቱን ለተቋሙ የበላይ ሃላፊ ሪፖርት ያደርጋል ፤ ተጽእኖ አድራጊው የበላይ ሃላፊ ሲሆን ጉዳዩን ለኮሚሽኑ ያሳውቃል፡፡
- በተቋሙ የስነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ችግሮች ላይ ሰራተኛው ወቅታዊ ውይይት እንዲያደርግ ለተቋሙ የበላይ ሃላፊ ያሳስባል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
- የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ህግ ተግባራዊ ለማድረግ በሚዘረጋው ሥርዓት መሠረት የሚመለከታቸው የመ/ቤቱ ሃላፊዎች ወይም ሰራተኞች ግዴታቸውን እንዲወጡ የተዘረጋውን ስርዓት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- የውስጥ ወይም የውጭ ኦዲተሮች እርምጃ እንዲወሰድባቸው ወይም እንዲስተካከሉ ሪፖርት ያቀረቡባቸው ጉዳዮች ፣ የዲስፕሊንና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች በትክክል መተግበራቸውን ይከታተላል፤ አፈጻጸሙን ለተቋሙ የበላይ ሃላፊና ለኮሚሽኑ ያሳውቃል፡፡
- ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት ግንባር ቀደም የሆኑ የተቋሙ ሠራተኞች ወይም ኃላፊ ከኮሚሽኑ በሚወጣ መስፈርት መሰረት መዝግቦ በመያዝ ለማበረታቻ ሽልማት እንዲታጩ ያደርጋል፡፡
- በየበጀት ዓመቱ ስለሚያከናውናቸው ተግባሮች የስራ መርሃ ግብርና የበጀት እቅድ አዘጋጅቶ ለተቋሙ የበላይ ሃላፊ ያቀርባል፣ እንዲሁም ለኮሚሽኑ ያሳውቃል ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ስለስራው አጠቃላይ ክንውን ለተቋሙ ኃላፊና እና ለኮሚሽኑ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- ስለሥራው አጠቃላይ ክንውን ለተቋሙ ኃላፊና ለኮሚሽኑ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- ተቋሙና ከሚሽኑ የሚሰጣቸውን ሌሎችም ለደንቡ አፈጻጸም የሚረዱ ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
|
| |
| የሥራ ሂደቱ አድራሻ፣ |
| |
- ስልክ 046 220 47 60 /የቢሮ/
- ሞባይል፣0911760248
- ፋክስ፣ 046 220 47 61
- ፖስታ፣ 311 /ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ/
|
| |
| |
| |
| |
|
  |